እንግዲህ ታማኝነታችሁ ተፈትኖ የሚረጋገጠው በዚህ ነው፤ ታናሽ ወንድማችሁ እስከሚመጣ ድረስ እንደማልለቃችሁ በንጉሡ በፈርዖን ስም እምላለሁ።
ዘፍጥረት 44:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተም ‘አየው ዘንድ ይዛችሁልኝ እንድትመጡ’ አልከን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከዚያም አንተ አገልጋዮችህን፣ ‘እንዳየው ወደ እኔ አምጡት’ አልኸን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም አንተ አገልጋዮችህን፥ ‘እንዳየው ወደ እኔ አምጡት’ አልኸን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም ለአገልጋዮችህ፦ ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም እጠብቀዋለሁ አልህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም ለባሪያዎችህ፦ ወደ እኔ አምጡት እኔም አየዋለሁ አልህ። |
እንግዲህ ታማኝነታችሁ ተፈትኖ የሚረጋገጠው በዚህ ነው፤ ታናሽ ወንድማችሁ እስከሚመጣ ድረስ እንደማልለቃችሁ በንጉሡ በፈርዖን ስም እምላለሁ።
ከዚህ በኋላ ታናሽ ወንድማችሁን ይዛችሁልኝ ኑ፤ በዚህ ዐይነት የተናገራችሁት ሁሉ እውነት መሆኑ ይረጋገጣል፤ ከመሞትም ትድናላችሁ።” እነርሱም በዚህ ነገር ተስማሙ፤
ዮሴፍ የእናቱ ልጅ የሆነውን ወንድሙን ብንያምን ባየው ጊዜ “ ‘ታናሽ ወንድም አለን’ ብላችሁ ነግራችሁኝ ነበር፤ ይህ እርሱ ነውን?” አለና “ልጄ፥ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለው።
እነሆ እኔ በእጅህ ላይ ያለውን ሰንሰለት ፈትቼ ነጻ አደርግሃለሁ፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን ለመውረድ ብትፈልግ እንደ ወደድክ አድርግ፤ እኔም ለአንተ እንክብካቤ አደርግልሃለሁ፤ ወደዚያ ለመሄድ ካልፈለግህ ግን መቅረት ትችላለህ፤ እነሆ አገሪቱ በሞላ በፊትህ ስለ ሆነች ወደ መረጥከው ቦታ መሄድ ትችላለህ።”
በጠላቶቻቸው እጅ ተማርከው ቢወሰዱም እዚያ እንዲገደሉ አደርጋለሁ፤ በዚህ ዐይነት እኔ በእነርሱ ላይ የማደርገው ትኲረት ይጐዳቸዋል እንጂ አይጠቅማቸውም።”