ነገር ግን አንድ ሌሊት እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦ አቤሜሌክን “ይህች ሴት ባለባል ስለ ሆነች እርስዋን በመውሰድህ ምክንያት ትሞታለህ” አለው።
ዘፍጥረት 41:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሁለት ዓመት በኋላ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ሕልም አየ፤ እርሱ በሕልሙ በዓባይ ወንዝ ዳር ቆሞ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድፍን ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ ፈርዖን ሕልም ዐለመ፤ በሕልሙም፣ በአባይ ወንዝ ዳር ቆሞ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድፍን ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ ፈርዖን ሕልም ዐለመ፤ በሕልሙም፥ በዐባይ ወንዝ ዳር ቆሞ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሁለት ዓመት በኋላም ፈርዖን ሕልምን አየ፤ እነሆም፥ በወንዙ ዳር ቆሞ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሁለት ዓመት በኍላም ፈርዖን ሕልምን አየ፥ እነሆም በወንዙ ዳር ቆሞ ነበረ። |
ነገር ግን አንድ ሌሊት እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦ አቤሜሌክን “ይህች ሴት ባለባል ስለ ሆነች እርስዋን በመውሰድህ ምክንያት ትሞታለህ” አለው።
የንጉሡ የወይን ጠጅ አሳላፊና የእንጀራ ቤት ኀላፊ ሁለቱም በእስር ቤት ሳሉ በአንድ ሌሊት ሕልም አዩ፤ የእያንዳንዳቸው ሕልም የተለያየ ትርጒም ነበረው።
በዚያኑ ሌሊት ንጉሡ እንቅልፍ አጥቶ ስለ ነበር በቤተ መንግሥቱ መዝገብ ላይ የሰፈሩትን የታሪክ ማስታወሻዎች አምጥተው ያነቡለት ዘንድ ትእዛዝ ሰጠ።
ከዚህም በኋላ ንጉሡ “ከዕብራውያን የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ እያነሣችሁ ዓባይ ወንዝ ውስጥ ጣሉ፤ ሴቶች ልጆች ግን በሕይወት ይኑሩ” ሲል ለሕዝቡ ጥብቅ ትእዛዝ አስተላለፈ።
እነዚህን ሁለት ተአምራት አይተው ባያምኑና ቃልህንም ባይሰሙ፥ ከዐባይ ወንዝ ጥቂት ውሃ ወስደህ በመሬት ላይ አፍስሰው፤ ከአባይ ወንዝ የወሰድከውም ውሃ በደረቀ ምድር ላይ ወደ ደም ይለወጣል።”
ልዑል እግዚአብሔር ለግብጽ ንጉሥ እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ በወንዝ ውስጥ የተጋደመ አስፈሪ የባሕር አውሬ የምትመስል አንተ! እነሆ፥ እኔ በቊጣ ተነሥቼብሃለሁ፤ ‘የዓባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ ይህን ወንዝ የሠራሁት እኔ ነኝ’ ትላለህ።
ግብጽም ባዶዋን ምድረ በዳ ሆና ትቀራለች። በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ። “ ‘አንተ የዓባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ ይህን ወንዝ የሠራሁት እኔ ነኝ’ ብለሃልና።
ከዚህም በላይ ጲላጦስ በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ፦ “በእርሱ ምክንያት ዛሬ ሌሊት በሕልም ብዙ ተሠቃይቻለሁና በዚያ በንጹሕ ሰው ላይ ምንም እንዳታደርግ” ስትል ላከችበት።
ይህች የምትወርሳት ምድር ከዚህ በፊት እንደ ነበርክባት እንደ ግብጽ ምድር አይደለችም። በግብጽ ምድር እህል ከዘራህ በኋላ እንደ ጓሮ አትክልት ማሳውን ውሃ ለማጠጣት ቦዩን በእግርህ አማካይነት ትቈጣጠረው ነበር።