Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 19:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በዓባይ ውስጥ ያለው ውሃ ዝቅ ይላል፤ ወንዙም ቀስ በቀስ ይደርቃል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የአባይ ወንዝ ይቀንሳል፤ ውሃውም እየጐደለ ይሄዳል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የዐባይ ወንዝ ይጎድላል፤ ወንዙም እያነሰም ይሄዳል ደረቅም ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ግብ​ፃ​ው​ያን ከባ​ሕር ውኃን ይጠ​ጣሉ፤ ወን​ዙም ያን​ሳል፤ ደረ​ቅም ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ውኆችም ከባሕር ይደርቃሉ፥ ወንዙም ያንሳል ደረቅም ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 19:5
9 Referencias Cruzadas  

“የሐይቅ ውሃ ተኖ እንደሚያልቅ፥ የወንዝም ፈሳሽ እንደሚደርቅ፥


የኒምሪም ወንዞች ደርቀዋል፤ ምንም ልምላሜ ሳይቀር በአጠገቡ ያለው ሣር ደርቆአል።


መንግሥታትን በማናወጥ የእግዚአብሔር ኀይል እስከ ባሕር ማዶ ደርሶአል፤ በከነዓንም ምድርም ያሉ ምሽጎች እንዲፈርሱ አዞአል።


በባዕዳን አገሮች ጒድጓዶችን ቆፍሬ ውሃ ጠጥቻለሁ፤ የብዙ ሠራዊቴ እግር የግብጽን ወንዞች አድርቋል’ ብለህ ተመክተሃል።


“እኔ በመጣሁ ጊዜ ማንም ሰው አለመኖሩ ለምንድን ነው? በጠራሁም ጊዜ ማንም ሰው መልስ ያልሰጠኝ ለምንድን ነው? እኔ ለመታደግ አልችልምን? ለማዳንስ ኀይል የለኝምን? በተግሣጼ ብቻ ባሕርን አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ወደ ምድረ በዳነት እለውጣለሁ፤ ዓሣዎቻቸውም ውሃ ከማጣት የተነሣ ሞተው ይበሰብሳሉ።


ስለዚህ እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “እኔ እናንተን እረዳለሁ፤ ባቢሎናውያንንም እበቀልላችኋለሁ፤ የባቢሎን የውሃ ምንጭና ወንዞችዋ ሁሉ እንዲደርቁ አደርጋለሁ።


የዓባይን ወንዝ ውሃ አደርቃለሁ፤ ግብጽም በክፉ ሰዎች ሥልጣን ሥር እንድትወድቅ አደርጋለሁ። ስለዚህም ባዕዳን ሕዝብ አገሪቱን በሞላ ያጠፋሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


በመከራ ባሕር ውስጥ ሲያልፉ እኔ እግዚአብሔር ማዕበሉን እመታለሁ፤ ጥልቅ የሆነውም የዓባይ ወንዝ ይደርቃል፤ ትዕቢተኛይቱ አሦር ትዋረዳለች፤ ግብጽም በትረ መንግሥትዋን ታጣለች።


ግብጻውያንም በዓሉን ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተው በእግዚአብሔር ፊት መቅረብ ባይፈልጉ፥ “ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተን የዳስ በዓል አናከብርም” በሚሉ መንግሥታት ላይ የሚደርሰው ቀሣፊ በሽታ ይመጣባቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos