በርከት ካሉ ዓመቶች በኋላ የሴዋ ልጅ የሆነችው የይሁዳ ሚስት ሞተች፤ ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከወዳጁ ከዐዱላማዊው ከሒራ ጋር በጎቹን ወደሚሸልቱ ሰዎች ወደ ቲምና ሄደ።
ዘፍጥረት 38:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ወራት ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ ሒራ ወደሚሉት ዐዱላማዊ ሰው ዘንድ ሄዶ መኖሪያውን እዚያ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ወራት ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ፣ ኤራ ወደ ተባለ ዓዶላማዊ ሰው ወረደ፤ እርሱም ዘንድ ለመኖር ቤቱ ገባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ወራት ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ፥ ኤራስ ወደ ተባለ ዓዶሎማዊ ሰው ወረደ፤ እርሱም ዘንድ ለመኖር ቤቱ ገባ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ወራት እንዲህ ሆነ፤ ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ ወረደ፤ ስሙ ኤራስ በሚባል በዓዶሎማዊውም ሰው ዘንድ አደረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ወራት እንዲህ ሆነ ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ ወረድ፥ ስሙን ኤራስ ወደሚሉት ወደ ዓዶሎማዊውም ሰው ገባ። |
በርከት ካሉ ዓመቶች በኋላ የሴዋ ልጅ የሆነችው የይሁዳ ሚስት ሞተች፤ ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከወዳጁ ከዐዱላማዊው ከሒራ ጋር በጎቹን ወደሚሸልቱ ሰዎች ወደ ቲምና ሄደ።
ይሁዳ በመያዥያ መልክ የሰጣትን ነገሮች ለማስመለስ የፍየል ጠቦት በዐዱላማዊው ሰው እጅ ወደ ሴትዮዋ ላከ፤ ሰውየው ግን ሊያገኛት አልቻለም።
በመከር ጊዜ መጀመሪያ ላይ ከሠላሳው ኀያላን በተለይ ሦስቱ ዳዊት ወዳለበት ወደ ዐዱላም ዋሻ ወረዱ፤ ከፍልስጥኤማውያን ሠራዊት ጥቂቱ ክፍል በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ነበር፤
አንድ ቀን ኤልሳዕ አንዲት ሀብታም ሴት ወደምትኖርበት ወደ ሱነም ሄደ፤ እርስዋም ምግብ እንዲበላ ጋበዘችው፤ ከዚያን ዕለት ጀምሮ ወደ ሱነም በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ በቤትዋ ይመገብ ነበር፤
ዳዊት ከጋት ከተማ ሸሽቶ በዐዱላም ከተማ አጠገብ ወደሚገኝው ወደ አንድ ዋሻ ሄደ፤ ወንድሞቹና ሌሎቹም ቤተሰቦቹ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደዚያ ሄደው ከእርሱ ጋር ተቀላቀሉ፤