ዘፍጥረት 36:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤላዕ በሞተ ጊዜ የቦጽራ አገር ተወላጅ የዘራሕ ልጅ ዮባብ በእርሱ እግር ተተክቶ ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባላቅ ሲሞት፣ የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ በምትኩ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤላዕ ሞተ፥ በስፍራውም የባሶራው የዛራ ልጅ ዮባብ ነገሠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባላቅም ሞተ፤ በእርሱ ፈንታም የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባላቅም ሞተ በስፍራውም የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ ኢዮባብም ሞተ |
ለመሥዋዕት የቀረቡ የበግና የፍየል ጠቦቶች በሚሠዉበት ጊዜ ደማቸውና ስባቸው ሰይፉን እንደሚሸፍን የእርሱም ሰይፍ በኤዶማውያን ደምና ስብ ይሸፈናል፤ እግዚአብሔር ይህን መሥዋዕት በቦጽራ ከተማ፥ ይህንንም ታላቅ ዕርድ በኤዶም ምድር ያቀርባል።
ከኤዶም ቦጽራ ቀይ መጐናጸፊያ ተጐናጽፎ የሚመጣው ይህ ማነው? በታላቅ ኀይሉ አስደናቂ ልብስ ለብሶ የሚራመደው ይህ ማነው? “ፍርድን የምሰጥ የማዳን ኀይል ያለኝ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
የቦጽራ ከተማ አስፈሪ ምድረ በዳ ሆና እንደምትቀር እኔ በራሴ ምዬአለሁ፤ ሕዝብ ሁሉ መቀለጃ ያደርጋታል፤ ስሟንም እንደ ርግማን ይቈጥሩታል። በአቅራቢያዋ ያሉ መንደሮች ሁሉ ለዘለዓለም ፍርስራሾች ሆነው ይቀራሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
ጠላት በቦጽራ ላይ ክንፉን በስፋት ዘርግቶ ወደ ታች እንደሚወርድ ንስር በመሆን ጉብ ይልባታል፤ በዚያን ጊዜ የኤዶም ወታደሮች በምጥ ተይዛ በፍርሃት እንደምትጨነቅ ወላድ ሴት ይሆናሉ።
“የእስራኤል ሕዝብ! በጎች በበረት፥ የበግ መንጋም በማሰማሪያ ቦታ እንደሚሰበሰብ በእርግጥ ከእስራኤል ሕዝብ የተረፉትን በአንድነት እሰበስባለሁ፤ ምድሪቱም በሕዝብ የተሞላች ትሆናለች” ይላል እግዚአብሔር።