ነገር ግን “ጒዳት ይደርስበታል” ብሎ ስለ ፈራ ያዕቆብ ከዮሴፍ ጋር ከአንድ እናት የወለደውን ልጁን ብንያምን ከወንድሞቹ ጋር ወደ ግብጽ አላከውም፤
ዘፍጥረት 35:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የራሔል ልጆች፥ ዮሴፍና ብንያም ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የራሔል ልጆች፦ ዮሴፍ፣ ብንያም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የራሔል ልጆች፥ ዮሴፍና ብንያም ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የራሔል ልጆች፤ ዮሴፍ፥ ብንያም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የራሔል ልጆች ዮሴፍ፥ ብንይም፤ |
ነገር ግን “ጒዳት ይደርስበታል” ብሎ ስለ ፈራ ያዕቆብ ከዮሴፍ ጋር ከአንድ እናት የወለደውን ልጁን ብንያምን ከወንድሞቹ ጋር ወደ ግብጽ አላከውም፤
ዮሴፍ የእናቱ ልጅ የሆነውን ወንድሙን ብንያምን ባየው ጊዜ “ ‘ታናሽ ወንድም አለን’ ብላችሁ ነግራችሁኝ ነበር፤ ይህ እርሱ ነውን?” አለና “ልጄ፥ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለው።
ለዮሴፍ ከቀረበለት ምግብ እየተወሰደ ይሰጣቸው ነበር፤ ለብንያም ግን ከሌሎቹ አምስት እጥፍ ተሰጠው፤ በዚህ ዐይነት ከዮሴፍ ጋር እስኪጠግቡ በልተው ጠጥተው ተደሰቱ።
ለዮሴፍ ዘሮች የተመደበው የምድሪቱ ደቡባዊ ክፍል በኢያሪኮ አጠገብ ከዮርዳኖስ ወንዝ ይጀምራል፤ ይኸውም ከኢያሪኮ ምንጮች ምሥራቃዊ ጫፍ በመነሣት ወደ በረሓው ይዘልቃል፤ ከኢያሪኮም ተነሥቶ ወደ ኮረብታማው አገር በመውጣት እስከ ቤትኤል ይደርሳል።
ቀድሞ ዐማሌቃውያን ይኖሩበት ከነበረው ከኤፍሬም ወታደሮች መጡ፤ ሌሎችም ከብንያም መጡ። ከማኪር መሪዎች፥ ከዛብሎንም በትረ መንግሥትን የሚይዙ መጡ።
በአደባባይ ተቀምጠው የነበሩት ሽማግሌዎችና ሌሎችም ሰዎች እንዲህ አሉ፥ “አዎ፥ እኛ ለዚህ ነገር ምስክሮች ነን፤ እግዚአብሔር ይህችን ሚስትህን ብዙ ልጆችን በመውለድ የያዕቆብን ቤት እንደ መሠረቱት እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርግልህ፤ እግዚአብሔር በኤፍራታ ያበልጽግህ፤ በቤተልሔምም ዝነኛ ያድርግህ፤