ዘፍጥረት 33:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔሳው በዙሪያው ተመልክቶ ሴቶቹንና ልጆቹን ባየ ጊዜ “እነዚህ ሁሉ ከአንተ ጋር ያሉ ሰዎች የማን ናቸው?” አለ። ያዕቆብም “ጌታዬ ሆይ፥ እነዚህ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” ሲል መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዔሳው ቀና ብሎ ሲመለከት ሴቶቹንና ልጆቹን አየ፤ እርሱም፣ “እነዚህ ዐብረውህ ያሉት እነማን ናቸው?” ብሎ ጠየቀው። ያዕቆብም መልሶ፣ “እነዚህማ እግዚአብሔር በቸርነቱ ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓይኑን አንስቶም ሴቶችንና ልጆችን ባየ ጊዜ፥ “እነዚህ ምኖችህ ናቸው?” አለ። እርሱም፦ “እግዚአብሔር ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሳውም ዐይኑን አነሣና ሴቶችንና ልጆችን አየ፤ እንዲህም አለ፥ “እነዚህ ምኖችህ ናቸው?” እርሱም፥ “እግዚአብሔር ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓይኑንም አነሣና ሴቶችንና ልጆችን አየ እንዲህም አለ፦ እነዚህ ምኖችህ ናቸው? እርሱም፦ እግዚአብሔር ለእኔ ለባሪያህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው አለ። |
ዮሴፍም “እነዚህ እግዚአብሔር በዚህ አገር ሳለሁ የሰጠኝ የእኔ ልጆች ናቸው” ብሎ ለአባቱ መለሰለት። ያዕቆብም “እባርካቸው ዘንድ ወደ እኔ አቅርብልኝ” አለው።