Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሩት 4:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በዚህ ሁኔታ ቦዔዝ ሩትን ሚስት አድርጎ ወደ ቤቱ ወሰዳት፤ በተገናኙም ጊዜ እግዚአብሔር ፀንሳ ወንድ ልጅ እንድትወልድ አደረጋት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ስለዚህ ቦዔዝ ሩትን ወሰዳት፤ ሚስቱም ሆነች። ከዚያም ወደ እርሷ ገባ፤ እግዚአብሔር እንድትፀንስ አደረጋት፤ ወንድ ልጅም ወለደች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ቦዔዝም ሩትን ወሰደ፥ ሚስትም ሆነችው፥ ወደ እርሷም ገባ፤ እግዚአብሔርም ፅንስ ሰጣት፥ ወንድ ልጅም ወለደች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ቦዔዝም ሩትን ወሰደ፥ ሚስትም ሆነችው፣ ደረሰባትም፥ እግዚአብሔርም ፅንስ ለጣት፥ ወንድ ልጅም ወለደች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ቦዔዝም ሩትን ወሰደ፤ ሚስትም ሆነችው፤ ደረስባትም፤ እግዚአብሔርም ፅንስ ሰጣት፤ ወንድ ልጅም ወለደች።

Ver Capítulo Copiar




ሩት 4:13
12 Referencias Cruzadas  

ዔሳው በዙሪያው ተመልክቶ ሴቶቹንና ልጆቹን ባየ ጊዜ “እነዚህ ሁሉ ከአንተ ጋር ያሉ ሰዎች የማን ናቸው?” አለ። ያዕቆብም “ጌታዬ ሆይ፥ እነዚህ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” ሲል መለሰ።


ልያ የራሔልን ያኽል እንዳልተወደደች እግዚአብሔር ባየ ጊዜ ልጅ መውለድ እንድትችል ማሕፀንዋን ከፈተላት፤ ራሔል ግን መኻን ሆነች፤


ልጄ ሆይ! አትፍሪ፤ ከእንግዲህ ወዲህ በከተማው ያሉ ሰዎች ሁሉ አንቺ መልካም ሴት መሆንሽን ያውቃሉ፤ የምትፈልጊውን ሁሉ አደርግልሻለሁ።


ልጆች ከእግዚአብሔር የሚገኙ ስጦታዎች ናቸው፤ እውነተኛም በረከት ናቸው።


መኻኒቱንም በቤቷ በክብር ያኖራታል፤ ልጆችንም በመስጠት ደስ ያሰኛታል። እግዚአብሔር ይመስገን!


ጠግበው የነበሩ ተርበው ለምግብ ተገዝተዋል፤ ተርበው የነበሩ ግን ጠግበዋል፤ መኻኒቱ ሰባት ወለደች፤ የብዙዎች ልጆች እናት የነበረችው ብቻዋን ቀረች።


የጸለይኩትም እግዚአብሔር ይህን ልጅ እንዲሰጠኝ ነበር፤ እግዚአብሔርም በጠየቅሁት መሠረት ይህን ወንድ ልጅ ሰጠኝ።


እግዚአብሔር ከዚህች ወጣት ሴት የሚሰጥህን ልጆች ይባርክልህ፤ ቤተሰብህንም ከይሁዳና ከትዕማር እንደተወለደው እንደ ፋሬስ ቤተሰብ ያድርግልህ።”


ያዕቆብም ራሔልን ተቈጥቶ “ልጅ ልሰጥሽና ልከለክልሽ የምችል እግዚአብሔር መሰልኩሽን?” አላት።


ርብቃ መኻን ስለ ነበረች ይስሐቅ ስለ እርስዋ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ስለ ሰማ ርብቃ ፀነሰች፤


ከዚያ በኋላ አብርሃም ለእግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቤሜሌክንና ሚስቱን፥ ሴቶች አገልጋዮቹንም ፈውሶአቸው ልጆች እንዲወልዱ አድርጎአቸዋል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios