ዘፍጥረት 33:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔሳው ግን ሊገናኘው ወደ እርሱ ሮጠ፤ በአንገቱም ላይ ተጠምጥሞ ዕቅፍ አድርጎ ሳመው፤ ሁለቱም ተላቀሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዔሳው ግን ሊገናኘው ወደ እርሱ ሮጦ ሄዶ ዐቀፈው፤ በዐንገቱም ላይ ተጠምጥሞ ሳመው፤ ሁለቱም ተላቀሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዔሳውም ሊገናኘው ሮጦ ተጠመጠመበት፥ አንገቱንም አቅፎ ሳመው፥ ተላቀሱም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሳውም ሊገናኘው ሮጠ፤ አንገቱንም አቅፎ ሳመው፤ ሁለቱም በአንድነት አለቀሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሳውም ሊገናኘው ሮጠ አንገቱንም አቅፎ ሳመው ተላቀሱም። |
ላባም የእኅቱ ልጅ ያዕቆብ መምጣቱን በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ፈጥኖ ሄደ፤ ዐቅፎ ከሳመውም በኋላ ወደ ቤት አመጣው፤ ያዕቆብ የሆነውን ሁሉ ለላባ ነገረው፤
ሰውየውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ከእግዚአብሔርም ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃል፤ ስለዚህ ስምህ ‘እስራኤል’ ይባላል” አለው።
ለዮሴፍ ከቀረበለት ምግብ እየተወሰደ ይሰጣቸው ነበር፤ ለብንያም ግን ከሌሎቹ አምስት እጥፍ ተሰጠው፤ በዚህ ዐይነት ከዮሴፍ ጋር እስኪጠግቡ በልተው ጠጥተው ተደሰቱ።
ስለዚህም ኢዮአብ ወደ ንጉሥ ዳዊት ሄደና አቤሴሎም ያለውን ሁሉ ነገረው፤ ንጉሡም አቤሴሎምን አስጠራ፤ አቤሴሎምም ሄዶ በንጉሡ ፊት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፤ ንጉሡም ሳመው።
እነሆ፥ አሁንም የእኔን ጸሎት ስማ፤ አንተን ማክበር የሚወዱትን የሌሎችንም አገልጋዮችህን ጸሎት አድምጥ፤ ዛሬ ልሠራው ያቀድኩት ይሳካልኝ ዘንድ የንጉሠ ነገሥቱን ልብ በማራራት እርዳኝ።” እነሆ፥ እኔ በዚህ ጊዜ የንጉሠ ነገሥቱ ወይን ጠጅ አሳላፊ ነበርኩ።
ገና በሩቅ ሳሉ ኢዮብን አዩት፤ ሆኖም እርሱ መሆኑን በቀላሉ ለይተው ሊያውቁት አልቻሉም። በሐዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ትቢያ ወደ ሰማይ እየበተኑና በራሳቸውም ላይ እየነሰነሱ በመጮኽ ማልቀስ ጀመሩ።
ልጁም ከሄደ በኋላ ዳዊት ከድንጋዩ ቊልል በስተኋላ ከተደበቀበት ስፍራ ወጥቶ በጒልበቱ በመንበርከክ ሦስት ጊዜ ወደ መሬት ሰገደ፤ እርሱና ዮናታን በሚሳሳሙበት ጊዜ ሁለቱም ያለቅሱ ነበር፤ ከዮናታንም ይልቅ የዳዊት ሐዘን የበረታ ነበር።