ዘፍጥረት 33:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጀመሪያ ሁለቱን ሴቶች አገልጋዮቹንና ልጆቻቸውን አስቀደመ፤ ቀጥሎ ልያንና ልጆችዋን አስከተለ፤ በመጨረሻም ራሔልንና ዮሴፍን ከሁሉ በኋላ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሁለቱን አገልጋዮች ከነልጆቻቸው አስቀደመ፤ ልያንና ልጆቿንም አስከተለ፤ ራሔልንና ዮሴፍን ግን ከሁሉ ኋላ እንዲሆኑ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴት አገልጋዮቹንና ልጆቻቸውንም ከፊት አደረገ፥ ልያንና ልጆችዋንም አስከተለ፥ ከዚያም ራሔልንና ዮሴፍን ከሁሉ በኋላ አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕቁባቶቹንና ልጆቻቸውንም በፊት አደረገ፤ ልያንና ልጆችዋን በኋላ፥ ራሔልንና ዮሴፍንም ከሁሉ በኋላ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዎችንና ልጆቻቸውንም በፊት አደረገ ልያንና ልጆችዋንም በኋለኛው ስፍራ ራሔልንና ዮሴፍንም ከሁሉ በኍላ አደረገ። |
ያዕቆብ ቀና ብሎ ሲመለከት፥ ዔሳው አራት መቶ ሰዎችን አስከትሎ ሲመጣ አየ፤ ያዕቆብም ልጆቹን ከልያ፥ ከራሔልና ከሁለቱ ሴቶች አገልጋዮቹ ጋር ከፋፈላቸው።
አሁን ግን ታላቂቱ ከተማችሁ በጣም ታፍራለች፤ እናት አገራችሁም ትዋረዳለች፤ ከመንግሥታት ሁሉ ያነሰች ትሆናለች። ውሃ የማይገኝባት ሆና ወደ ምድረ በዳነት ትለወጣለች።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነርሱ የእኔ ይሆናሉ፤ እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ የግሌ ይሆናሉ፤ ወላጆች ለሚያገለግሉአቸው ልጆች ምሕረት እንደሚያደርጉላቸው እኔም ለእነርሱ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ።