ዘፍጥረት 32:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ በጒዞ ላይ ሳለ የእግዚአብሔር መላእክት በመንገድ ተገናኙት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም ጕዞውን ቀጠለ፤ የእግዚአብሔርም መላእክት ተገናኙት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም መንገዱን ሄደ፥ የእግዚአብሔር መላእክትም አጋጠሙት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም መንገዱን ሄደ፤ በዐይኖቹም የእግዚአብሔርን ሠራዊት ከትመው አየ፤ የእግዚአብሔር መላእክትም ተገናኙት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም መንገዱን ሄደ የእግዚአብሔር መላእክትም ተገናኙት። |
ጳውሎስም ቢሆን አጵሎስም ቢሆን፥ ጴጥሮስም ቢሆን፥ ዓለምም ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ ሞትም ቢሆን፥ አሁን ያለውም ቢሆን፥ በኋላ የሚመጣውም ቢሆን፥ ሁሉም የእናንተ ነው።
ይህም የሆነው በአሁኑ ዘመን በቤተ ክርስቲያን አማካይነት በሰማይ ያሉት አለቆችና ባለሥልጣኖች የእግዚአብሔርን ጥበብ በየመልኩ እንዲያውቁ ነው።