ዘፍጥረት 29:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልያ ዐይነ ልም ስትሆን፥ ራሔል ግን ቁመናዋ የሚያምር የደስ ደስ ያላት ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልያ ዐይነ ልም ስትሆን ራሔል ግን ቁመናዋ ያማረ መልኳም የተዋበ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልያም ዓይነ ልም ነበረች፥ ራሔል ግን መልከ መልካም ነበረች ፊትዋም ውብ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልያም ዓይነ ልም ነበረች፤ ራሔል ግን መልከ መልካም ነበረች፥ ፊቷም ውብ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልያም ዓይነ ልም ነበረች፤ ራሔል ግን መልከ መልካም ነበረች ፊትዋም ውብ ነበረ። |
የዚያ አገር ሰዎችም ስለ ርብቃ “ምንህ ናት” ብለው በጠየቁት ጊዜ “እኅቴ ናት” አላቸው፤ ይህንንም ያለበት ምክንያት ርብቃ በጣም ቈንጆ ስለ ነበረች የዚያ አገር ሰዎች በእርስዋ ሰበብ እንዳይገድሉት በመፍራት ነው።
ስለዚህ ጶጢፋር ያለውን ንብረት ሁሉ በዮሴፍ ቊጥጥር ሥር አደረገ፤ ጶጢፋር ከሚመገበው ምግብ በስተቀር የሚያውቀው ምንም ነገር አልነበረም። ዮሴፍ ቁመናው የተስተካከለ መልከ መልካም ሰው ነበር።
ከመስጴጦምያ ስመለስ በከነዓን ምድር ገና ከኤፍራታ ሳልርቅ እናትህ ራሔል ሞተችብኝ፤ እርስዋን ወደ ኤፍራታ በሚወስደው መንገድ ዳር ቀበርኋት።” (ይህችም ኤፍራታ ዛሬ ቤተልሔም ተብላ የምትጠራው ቦታ ነች።)
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ ታለቅሳለች፤ ልጆችዋ በሕይወት ስለሌሉ መጽናናትን እምቢ አለች።
ዛሬ ከእኔ ተለይተህ በምትሄድበት ጊዜ፥ በብንያም ግዛት በሚገኘው ጼልጻሕ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ባለው በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ፤ እነርሱም ስትፈልጋቸው የነበሩ አህዮች መገኘታቸውንና አባትህም ስለ እነርሱ ማሰቡን ትቶ ስለ አንተ በመጨነቅ ‘እንግዲህ ስለ ልጄ ምን ላድርግ’ እያለ በመጠየቅ ላይ መሆኑን ይነግሩሃል።