ይኸውም እኔ በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳትመርጥ በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ፤
ዘፍጥረት 26:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔሳው አርባ ዓመት ሲሆነው የብኤሪን ልጅ ዮዲትንና የኤሎንን ልጅ ባሴማትን አገባ፤ ሁለቱም ሒታውያን ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዔሳው አርባ ዓመት በሆነው ጊዜ፣ የኬጢያዊውን የብኤሪን ልጅ ዮዲትን እንዲሁም የኬጢያዊውን የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትን አገባ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የሒታውያዊ የብኤሪን ልጅ ዮዲትን፥ የሒታውያዊ የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የኬጢያዊው የብኤልን ልጅ ዮዲትን፥ የኬጢያዊው የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የኬጢያዊ የብኤሪን ልጅ ዮዲትን የኬጢያዊ የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ |
ይኸውም እኔ በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳትመርጥ በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ፤
ርብቃ ይስሐቅን “ዔሳው ባገባቸው በእነዚህ በሒታውያን ሴቶች ምክንያት መኖሬን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ደግሞ ከነዚህ ከሒታውያን ሴቶች አንዲቱን ካገባ ከመኖር ይልቅ ሞቴን እመርጣለሁ” አለችው።
ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንዶች ልጆቻችሁ ሚስቶች ብታደርጉ የእነዚያ ሴቶች ልጆች ጣዖት ማምለክን ስለሚከተሉ የእናንተንም ወንዶች ልጆች ጣዖት አምልኮን እንዲከተሉ ያደርጓቸዋል።
ከዚህም በኋላ ዳዊት ሒታዊውን አቤሜሌክንና ከጸሩያ ልጆች የኢዮአብን ወንድም አቢሳን “ከእናንተ ከሁለታችሁ ከእኔ ጋር አብሮ ወደ ሳኦል ሰፈር የሚሄድ ማን ነው?” ሲል ጠየቃቸው። አቢሻይም “እኔ እሄዳለሁ” ሲል መለሰ።