Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 7:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ነገር ግን ከዝሙት ለመራቅ እያንዳንዱ ወንድ የራሱ ሚስት ትኑረው፤ እያንዳንዱዋም ሴት የራስዋ ባል ይኑራት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ነገር ግን ከዝሙት ለመጠበቅ፣ እያንዳንዱ ሰው የራሱ ሚስት ትኑረው፤ እያንዳንዷም ሴት የራሷ ባል ይኑራት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ነገር ግን ከዝሙት ለመራቅ እያንዳንዱ ወንድ ለራሱ ሚስት ትኑረው፤ እያንዳንዱዋም ሴት ለራስዋ ባል ይኑራት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ነገር ግን እን​ዳ​ት​ሴ​ስኑ ሰው ሁሉ በሚ​ስቱ ይወ​ሰን፤ ሴትም ሁላ በባ​ልዋ ትወ​ሰን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 7:2
14 Referencias Cruzadas  

እንዲሁም ባሎች የገዛ ራሳቸውን እንደሚወዱ ሚስቶቻቸውን መውደድ ይገባቸዋል፤ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል።


ነገር ግን ይህ ነገር እናንተንም ይመለከታል፤ ስለዚህ ባል ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ ይውደድ፤ ሚስትም ባልዋን ታክብር።


ነገር ግን በሥጋ ምኞት ከመቃጠል ይልቅ ማግባት የተሻለ ነውና ራሳቸውን መቈጣጠር ቢያቅታቸው ያግቡ።


ሚስት ከእግዚአብሔር የምትሰጥ በረከት ስለ ሆነች ሚስት ካገኘህ መልካም ነገር አግኝተሃል ማለት ነው፤


ስለዚህ ከዝሙት ራቁ፤ ሰው የሚያደርገው ሌላው ኃጢአት ሁሉ ከሰውነቱ ውጪ የሚደረግ ነው፤ ዝሙትን የሚፈጽም ሰው ግን በገዛ ሰውነቱ ላይ ኃጢአት ይሠራል፤


እንደእነዚህ ያሉት ሰዎች ጋብቻን ይከለክላሉ፤ የሚያምኑና እውነትን የሚያውቁ ሰዎችም እርሱን እያመሰገኑ እንዲመገቡት እግዚአብሔር የፈጠረላቸውን ምግብ “አትብሉ” እያሉ ይከለክላሉ።


“ስለምን መሥዋዕታችንን አይቀበልም?” ብላችሁ ትጠይቃላችሁ፤ እግዚአብሔር መሥዋዕታችሁን የማይቀበለው የቃል ኪዳን ጓደኞቻችሁ ለሆኑት ለወጣትነት ሚስቶቻችሁ ታማኝነታችሁን ስላፈረሳችሁ ነው፤ በእናንተም መካከል እግዚአብሔር ምስክር ነበር።


አንድ ሰው ቤትና ሀብት ከወላጆቹ ሊወርስ ይችላል፤ አስተዋይ ሚስትን የሚሰጥ ግን እግዚአብሔር ብቻ ነው።


እኔ ግን “በዝሙት ምክንያት ካልሆነ በቀር፥ ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ እንድታመነዝር ያደርጋታል፤ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ አመንዝራ ይሆናል” እላችኋለሁ።


ስለ ጻፋችሁልኝ ጥያቄ ሰው ከሴት ጋር ግንኙነት ባያደርግ መልካም ነው።


ባል ለሚስቱ ማድረግ የሚገባውን የጋብቻ መብትዋን አይከልክላት፤ እንዲሁም ሚስት ለባልዋ ማድረግ የሚገባትን የጋብቻ መብቱን አትከልክለው።


ከእናንተ እያንዳንዱ ሚስቱን በቅድስናና በክብር ጠብቆ መያዝን ይወቅ።


አባቶቻቸውም ሆኑ ወንድሞቻቸው ወደ እናንተ መጥተው ሊቃወሙአችሁ ቢፈልጉ ‘ሚስቶች ለማድረግ የወሰድናቸው በጦርነት አስገድደን ስላልሆነ እባካችሁ ምሕረት አድርጉልን፤ እናንተም በፈቃዳችሁ ስላልሰጣችሁን መሐላችሁን በማፍረስ በደለኞች አትሆኑም’ ብላችሁ መልስ መስጠት ትችላላችሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios