ዘፍጥረት 24:62 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ ይስሐቅ “ብኤር ላሐይ ሮኢ ወይም የሚያየኝ ሕያው አምላክ” የተባለው ኲሬ ወዳለበት በረሓ መጥቶ በኔጌብ ተቀምጦ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ፣ ይሥሐቅ በኔጌብ ይኖር ስለ ነበር፣ ከብኤርላሃይሮኢ መጥቶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይስሐቅም ብኤርለሃይሮኢ በሚሉአት ምንጭ መንገድ መጣ፥ በአዜብ ምድር ተቀምጦ ነበርና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይስሐቅም በዐዘቅተ ራእይ በኩል ወደ ምድረ በዳ ይመለከት ነበር፤ በአዜብ በኩል ባለው ምድር ተቀምጦ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይስሐቅም ብኤርለሃይሮኢ በሚሉአት ምንጭ መንገድ መጣ በአዜብ ምድር ተቀምጦ ነበርና። |
ስለዚህ ሰዎች በቃዴስና በባሬድ መካከል የሚገኘውን የውሃ ጒድጓድ “ብኤር ላሐይ ሮኢ” ብለው ይጠሩታል፤ ትርጒሙም “ሕያው የሆነውና የሚያየኝ አምላኬ ጒድጓድ” ማለት ነው።
ከዚህ በኋላ ርብቃ ከደንገጡሮችዋ ጋር ለመሄድ ተነሣች፤ በግመሎቹ ላይ ተቀምጠው ከአብርሃም አገልጋይ ጋር ለመሄድ ተዘጋጁ። በዚህ ዐይነት የአብርሃም አገልጋይ ርብቃን ይዞ ሄደ።
አብርሃም ከሞተ በኋላ ልጁን ይስሐቅን እግዚአብሔር ባረከው፤ ይስሐቅም “ብኤርላሐይ ሮኢ ወይም የሚያየኝ ሕያው አምላክ” ተብሎ በሚጠራው ኲሬ አጠገብ ይኖር ነበር።