አብራምም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ጌታ አምላክ ሆይ፥ ምንም ልጅ ስለሌለኝ የምትሰጠኝ በረከት ምን ያደርግልኛል? ሀብቴን የሚወርሰው የደማስቆ ሰው የሆነው ኤሊዔዘር ነው።
ዘፍጥረት 24:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃም የንብረቱ ሁሉ ኀላፊ በመሆን ለረዥም ዘመን የኖረውን አገልጋዩን እንዲህ አለው፤ “እጅህን በጒልበቴ ላይ አድርገህ ማልልኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብርሃም የንብረቱ ሁሉ ኀላፊ፣ የቤቱ ሁሉ አዛዥ የሆነውን አረጋዊ አገልጋዩን እንዲህ አለው፤ “እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም ሎሌውን የቤቱን ሽማግሌ የከብቱን ሁሉ አዛዥ አለው፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም ሎሌውን፥ የቤቱን ሽማግሌ፥ የከብቱን ሁሉ አዛዥ አለው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም ሎሌውን የቤቱን ሽማግሌ የከብቱን ሁሉ አዛዥ አለው፦ |
አብራምም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ጌታ አምላክ ሆይ፥ ምንም ልጅ ስለሌለኝ የምትሰጠኝ በረከት ምን ያደርግልኛል? ሀብቴን የሚወርሰው የደማስቆ ሰው የሆነው ኤሊዔዘር ነው።
ዮሴፍ የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘው፤ “ለመጫን የሚችሉትን ያኽል በየስልቻዎቻቸው ሙላላቸው፤ የእያንዳንዱንም ገንዘብ በየስልቻው አፍ አስቀምጠው።
ያዕቆብ የሚሞትበት ቀን በተቃረበ ጊዜ ልጁን ዮሴፍን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “በፊትህ ሞገስን አግኝቼ ከሆነ፥ በምሞትበት ጊዜ በግብጽ ምድር እንዳትቀብረኝ፥ እጅህን በጒልበቴ ላይ አኑረህ በመሐላ ቃል ግባልኝ።
ያዕቆብም “ይህን እንደምታደርግ በመሐላ ቃል ግባልኝ” አለው። ዮሴፍ ይህንኑ በመሐላ አረጋገጠለት፤ ያዕቆብም በመኝታው ላይ እንዳለ በመስገድ እግዚአብሔርን አመሰገነ።
የቤተ መንግሥቱ ባለሟሎች ወደ እርሱ ቀርበው ከመሬት ላይ ሊያስነሡት ሞከሩ፤ እርሱ ግን ከመሬት ላለመነሣትና ከእነርሱም ጋር ምንም ነገር ላለመቅመስ ወሰነ፤
የሠረገላዎቹ እኩሌታ ኀላፊ የሆነ ዚምሪ ተብሎ የሚጠራ ከጦር መኰንኖቹ አንዱ በንጉሡ ላይ ዐደመ፤ አንድ ቀን ኤላ በቲርጻ ከተማ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በሆነው አርጻ ተብሎ በሚጠራው ባለሟሉ ቤት ብዙ መጠጥ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር።