La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 21:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አብርሃም ሚስቱ ሣራ የወለደችለትን ልጅ “ይስሐቅ” ብሎ ስም አወጣለት፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አብርሃም፣ ሣራ የወለደችለትን ልጅ ስሙን ይሥሐቅ አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አብርሃምም የተወለደለትን ሣራ የወለደችለትን የልጁን ስም ይስሐቅ ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አብ​ር​ሃ​ምም ሣራ የወ​ለ​ደ​ች​ለ​ትን የል​ጁን ስም ይስ​ሐቅ ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አብርሃምም የተወለደለትን ሣራ የወለደችለትን የልጁን ስም ይስሐቅ ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 21:3
11 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እንዲህስ አይሆንም፤ ነገር ግን ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ትለዋለህ፤ ቃል ኪዳኔን ከእርሱና ከዘሩ ጋር ለዘለዓለም አጸናለሁ፤


ነገር ግን የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ከሣራ ከሚወለደው ልጅህ ከይስሐቅ ጋር ቃል ኪዳኔን አጸናለሁ።”


እግዚአብሔር ግን አብርሃምን “ስለ ልጁና ስለ አገልጋይቱ ስለ አጋር አትጨነቅ፤ ዘር የሚወጣልህ በይስሐቅ በኩል ስለ ሆነ ሣራ የምትልህን ሁሉ አድርግ፤


ሣራ “እግዚአብሔር ደስታና ሳቅ አመጣልኝ፤ ስለዚህ ይህን ነገር የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋር ይስቃል” አለች።


እግዚአብሔርም “የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እዚያ በማሳይህ አንድ ኮረብታ ላይ እርሱን መሥዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ” አለው።


የአብርሃም ልጅ የይስሐቅ ታሪክ ይህ ነው፤ አብርሃም ይስሐቅን ወለደ።


አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅ ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብ ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤


የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ ስለዚህ አብርሃም ይስሐቅን በወለደ ጊዜ በስምንተኛው ቀን ገረዘው፤ እንዲሁም ይስሐቅ ልጁን ያዕቆብን ገረዘው። ያዕቆብም የነገድ አባቶች የሆኑትን ዐሥራ ሁለቱን ልጆቹን ገረዘ።


እንዲሁም የአብርሃም ዘር ሁሉ የአብርሃም ልጆች ናቸው ማለት አይደለም። እግዚአብሔር አብርሃምን “ዘር የሚወጣልህ በይስሐቅ ነው” ስላለው ነው፤


ታዲያ፥ እግዚአብሔር፥ “በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል” ብሎት ነበር።


ከዚህም በኋላ የቀድሞ አባታችሁን አብርሃምን ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ከሚገኘው ምድር ጠርቼ፥ በከነዓን ምድር ሁሉ መራሁት፤ ዘሩንም አበዛሁለት፤ ይስሐቅንም ሰጠሁት፤