Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 9:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እንዲሁም የአብርሃም ዘር ሁሉ የአብርሃም ልጆች ናቸው ማለት አይደለም። እግዚአብሔር አብርሃምን “ዘር የሚወጣልህ በይስሐቅ ነው” ስላለው ነው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከአብርሃም ዘርም ስለ ሆኑ፣ ሁሉም ልጆቹ አይደሉም፤ ይልቁንስ፣ “ዘርህ በይሥሐቅ በኩል ይጠራልሃል” እንደ ተባለው ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የአብርሃም ዘር ስለ ሆኑ ሁሉም የእርሱ ልጆች ናቸው ማለት አይደለም፤ ነገር ግን “ዘርህ በይስሐቅ ይጠራልሃል፤” ተባለ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የአ​ብ​ር​ሃም ዘር ሁሉ ልጆቹ የሆ​ኑት አይ​ደ​ለም፤ ከይ​ስ​ሐቅ ዘር ይጠ​ራ​ል​ሃል አለው እንጂ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ነገር ግን፦ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል ተባለ።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 9:7
11 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ግን አብርሃምን “ስለ ልጁና ስለ አገልጋይቱ ስለ አጋር አትጨነቅ፤ ዘር የሚወጣልህ በይስሐቅ በኩል ስለ ሆነ ሣራ የምትልህን ሁሉ አድርግ፤


ታዲያ፥ እግዚአብሔር፥ “በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል” ብሎት ነበር።


የአገልጋይቱ ልጅ የተወለደው በሥጋዊ ልማድ ሲሆን የነፃይቱ ልጅ የተወለደው ግን በተሰጠው ተስፋው ቃል መሠረት ነበር።


እኛ እግዚአብሔርን በመንፈስ የምናመልክና በውጭ በሚታየው ሥርዓት ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ የምንመካ ስለ ሆንን በእውነት ተገርዘናል።


ይልቁንስ ንስሓ መግባታችሁን የሚያመለክት ሥራ ሥሩ እንጂ እኛ የአብርሃም ልጆች ነን እያላችሁ በልባችሁ አትመኩ። እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እንደሚችል እነግራችኋለሁ።


እነርሱ ግን “እኛ የአብርሃም ዘር ነን፤ ከቶ ለማንም ባሪያ ሆነን አናውቅም፤ ታዲያ፥ አንተ ‘ነጻ ትወጣላችሁ’ የምትለን እንዴት ነው?” አሉት።


ሀብታሙም ሰው ‘አይደለም! አባት አብርሃም ሆይ፥ አንድ ሰው ከሞት ተነሥቶ ቢሄድና ቢነግራቸው ግን ተጸጽተው ንስሓ ይገባሉ’ አለ።


‘እኛ የአብርሃም ልጆች ነን’ በማለት የምታመልጡ አይምሰላችሁ፤ እግዚአብሔር ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆችን ሊያስነሣለት ይችላል እላችኋለሁ።


ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተም እንደ ይስሐቅ የተስፋው ቃል ልጆች ናችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios