Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 21:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አብርሃም፣ ሣራ የወለደችለትን ልጅ ስሙን ይሥሐቅ አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 አብርሃምም የተወለደለትን ሣራ የወለደችለትን የልጁን ስም ይስሐቅ ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 አብርሃም ሚስቱ ሣራ የወለደችለትን ልጅ “ይስሐቅ” ብሎ ስም አወጣለት፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 አብ​ር​ሃ​ምም ሣራ የወ​ለ​ደ​ች​ለ​ትን የል​ጁን ስም ይስ​ሐቅ ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 አብርሃምም የተወለደለትን ሣራ የወለደችለትን የልጁን ስም ይስሐቅ ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 21:3
11 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ይሁን ዕሺ፤ ነገር ግን ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይሥሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፤ እኔም ከርሱ በኋላ ለዘሩ ሁሉ የሚሆን የዘላለም ኪዳን ከርሱ ጋራ እገባለሁ።


ከአብርሃም ዘርም ስለ ሆኑ፣ ሁሉም ልጆቹ አይደሉም፤ ይልቁንስ፣ “ዘርህ በይሥሐቅ በኩል ይጠራልሃል” እንደ ተባለው ነው።


ሣራም፣ “እግዚአብሔር ሣቅ አድሎኛል፤ ስለዚህ፣ ይህን የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋራ ይሥቃል” አለች።


ይህም እግዚአብሔር፣ “ዘርህ በይሥሐቅ ይጠራል” ያለለት ነበር።


አብርሃም ይሥሐቅን ወለደ፤ ይሥሐቅ ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብ ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤


እኔ ግን አባታችሁን አብርሃምን ከወንዙ ማዶ ካለው ምድር አምጥቼ፣ በከነዓን ምድር ሁሉ መራሁት፤ ዘሮቹን አበዛሁለት፤ ይሥሐቅንም ሰጠሁት።


ከዚያም የግዝረትን ኪዳን ሰጠው፤ አብርሃምም ይሥሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛውም ቀን ገረዘው። ይሥሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን የነገድ አባቶች ወለደ።


እግዚአብሔርም፣ “የምትወድደውን አንዱን ልጅህን፣ ይሥሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እኔ በማመለክትህ በአንዱ ተራራ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው” አለው።


እግዚአብሔርም አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “ስለ ልጁም ሆነ ስለ አገልጋይህ ሐሳብ አይግባህ፤ ዘር የሚጠራልህ በይሥሐቅ በኩል ስለ ሆነ፣ ሣራ የምትልህን ሁሉ ስማ።


ኪዳኔን ግን የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ልጅ፣ ከይሥሐቅ ጋራ አደርጋለሁ።”


የአብርሃም ልጅ የይሥሐቅ ትውልድ ይህ ነው። አብርሃም ይሥሐቅን ወለደ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios