ዘፍጥረት 20:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃም ሚስቱን ሣራን እኅቴ ናት አለ፤ ስለዚህ የገራራ ንጉሥ አቤሜሌክ ሰዎች ልኮ ሣራን እንዲያመጡለት አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም አብርሃም ሚስቱን ሣራን፣ “እኅቴ ናት” ይል ነበር። ስለዚህ የጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክ መልእክተኛ ልኮ ሣራን ወሰዳት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃም ሚስቱን ሣራን፦ “እኅቴ ናት” አለ፥ የገራርም ንጉሥ አቢሜሌክ በመልክተኛ ሣራን ወሰዳት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም ሚስቱን ሣራን “እኅቴ ናት” አላቸው፤ የከተማዪቱ ሰዎች ስለ እርስዋ እንዳይገድሉት “ሚስቴ” ናት ማለትን ፈርቶአልና፤ የጌራራ ንጉሥ አቤሜሌክም ላከና ሣራን ወሰዳት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም ሚስቱን ሣራም፤ እኅቴ ናት አለ የጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክም ላከና ሣራን ወሰዳት። |
በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ራብ ሌላ ዳግመኛ ራብ በምድር ላይ መጣ፤ በዚህ ምክንያት ይስሐቅ የፍልስጥኤማውያን ንጉሥ አቤሜሌክ ወዳለበት ወደ ገራር ሄደ፤
የዚያ አገር ሰዎችም ስለ ርብቃ “ምንህ ናት” ብለው በጠየቁት ጊዜ “እኅቴ ናት” አላቸው፤ ይህንንም ያለበት ምክንያት ርብቃ በጣም ቈንጆ ስለ ነበረች የዚያ አገር ሰዎች በእርስዋ ሰበብ እንዳይገድሉት በመፍራት ነው።
የሐናኒ ልጅ የሆነው ኢዩ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ለመገናኘት መጥቶ እንዲህ ሲል ገሠጸው፤ “አንተ ክፉዎችን መርዳትና እግዚአብሔርን ከሚጠሉት ጋር መተባበር መልካም ይመስልሃልን? ይህ ያደረግኸው ክፉ ነገር የእግዚአብሔር ቊጣ በአንተ ላይ እንዲወርድ አድርጎአል፤
ነገር ግን የማሬሻ ተወላጅ የሆነው የዶዳዋ ልጅ ኤሊዔዘር ኢዮሣፍጥን “ከአካዝያስ ጋር የስምምነት ውል ስላደረግህ እግዚአብሔር የሠራኸውን ሁሉ ያጠፋል” ሲል አስጠንቅቆት ስለ ነበር መርከቦቹ በሙሉ ተሰባበሩ፤ ከቶም በባሕር ላይ አልተጓዙም።
ነገር ግን የባቢሎን መልእክተኞች በአገሪቱ ስለ ተደረገው አስደናቂ ነገር ሊጠይቁት ወደ እርሱ መጥተው በነበረ ጊዜ እግዚአብሔር በሕዝቅያስ ልብ ውስጥ ያለውን ሐሳብ ለማወቅ ይፈትነው ዘንድ ተወው።