Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መክብብ 7:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ምንም ስሕተት ሳይፈጽም ሁልጊዜ መልካም ነገርን የሚሠራ ደግ ሰው በምድር ላይ አይገኝም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ትክክለኛውን ነገር የሚያደርግና ፈጽሞ ኀጢአት የማይሠራ ጻድቅ ሰው በምድር ላይ የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በምድር ላይ መልካምን የሚሠራ፥ ምንም ኃጢአት የማያደርግ ጻድቅ አይገኝምና።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 በም​ድር ላይም መል​ካ​ምን የሚ​ሠራ ኀጢ​አ​ት​ንም የማ​ያ​ደ​ርግ ጻድቅ ሰው አይ​ገ​ኝ​ምና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 በምድር ላይ መልካምን የሚሠራ ኃጢአትንም የማያደርግ ጻድቅ አይገኝምና።

Ver Capítulo Copiar




መክብብ 7:20
16 Referencias Cruzadas  

ሰዎች ሁሉ ኃጢአት ሠርተዋል፤ እግዚአብሔር የሰጣቸውንም ክብር አጥተዋል።


ሁላችንም እንደ በጎች ባዝነን ነበር፤ ሁላችንም ወደ ራሳችን መንገድ ሄደን ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ።


እኛ ሁላችን ብዙ ጊዜ እንሳሳታለን፤ በንግግሩ የማይሳሳት እርሱ ሰውነቱን መቈጣጠር የሚችል ፍጹም ሰው ነው።


“መቼም በደል የማይሠራ የለምና ሕዝብህ ኃጢአት በመሥራት አንተን ሲያሳዝኑህ፥ አንተም ተቈጥተህ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና ወደ ሌላ አገር ማርከው እንዲወስዱአቸው በምትፈቅድበት ጊዜ፥ ምንም እንኳ ያ አገር ሩቅ ቢሆን፥


“ኅሊናዬ ንጹሕ ነው፤ ኃጢአትም የለብኝም” ማለት የሚችል ሰው ይኖራልን?


“መቼም በደል የማይሠራ ሰው የለምና ሕዝብህ እስራኤላውያን ኃጢአት በመሥራት አንተን ቢያሳዝኑህ፥ አንተም ተቈጥተህ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና ወደ ሌላ አገር ማርከው እንዲወስዱአቸው በምትፈቅድበት ጊዜ፥ ያ አገር ሩቅ ቢሆንም እንኳ፥


እኛ ሁላችን በኃጢአት ረክሰናል፤ ጽድቃችንም እንደ አደፍ ጨርቅ ሆኖአል፤ ከኃጢአታችን ብዛት የተነሣ ደርቀው በነፋስ እንደሚረግፉ ቅጠሎች ሆነናል።


በአንተ ፊት ማንም ጻድቅ ሰው ስለሌለ እኔን አገልጋይህን ለፍርድ አታቅርበኝ።


ኃጢአታችንን ብትከታተል ማን ከፍርድ ሊያመልጥ ይችላል?


“ኢዮብ ሆይ! ይህ ንግግርህ ስሕተት መሆኑን ልገልጥልህ እወዳለሁ፤ እግዚአብሔር ከሰው ሁሉ ይበልጣል።


ካህኑ ያን ሰው ይመርምር፤ ቋቁቻ ያለበትም ስፍራ ደብዘዝ ያለ ነጭ ቢሆን ብዙ ጒዳት የማያመጣ በቈዳ ላይ የሚታይ ሽፍታ ስለ ሆነ ያ ሰው ንጹሕ ነው።


ዮናታንም በቊጣ ከማእዱ ላይ ተነሣ፤ በዚያ ቀን ማለትም አዲስ ጨረቃ በታየችበት በዓል በሁለተኛ ቀን ምንም ምግብ አልበላም፤ ሳኦል ዳዊትን በማዋረዱ ምክንያት ስለ ዳዊት ሁኔታ ዮናታን በብርቱ አዝኖ ነበር።


ሞኞች በልባቸው፦ “እግዚአብሔር የለም” ይላሉ፤ እንደነዚህ ያሉት የተበላሹ ናቸው፤ አጸያፊ ድርጊቶችንም ይፈጽማሉ፤ ከእነርሱ መካከል መልካም ነገርን የሚያደርግ አንድም የለም።


ነገር ግን ሁሉም ባዝነዋል፤ ሁሉም በአንድነት ተበላሽተዋል፤ ከእነርሱ አንድ እንኳ መልካም ነገርን የሚያደርግ የለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios