ዘፍጥረት 18:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀና ብሎም ሲመለከት ሦስት ሰዎች እዚያ ቆመው አየ፤ እንዳያቸውም ወዲያውኑ ሊያነጋግራቸው ወደ እነርሱ ሮጠ፤ ግንባሩም መሬት እስኪነካ ዝቅ ብሎ በመስገድ እጅ ነሣ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀና ብሎም ሲመለከት፣ ሦስት ሰዎች ቆመው አየ፤ ወዲያውም ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ፣ ፈጥኖ ወደ ሰዎቹ ሄደ፤ ወደ መሬት ዝቅ ብሎም እጅ ነሣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፥ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ፥ እንዲህም አለ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐይኑንም በአነሣ ጊዜ እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድርም ሰገደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓይኑንም አነሣና እነሆ ሦስት ስዎች በፊቱ ቆመው አየ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ እንዲህም አለ፥ |
በዚያኑ ምሽት ሁለቱ መላእክት ወደ ሰዶም መጡ፤ በዚያን ጊዜ ሎጥ በከተማይቱ በር ተቀምጦ ነበር፤ መላእክቱን ባያቸው ጊዜ ሊያነጋግራቸው ከተቀመጠበት ተነሥቶ ሄደ፤ ጐንበስ ብሎም እጅ ነሣቸውና፥
ዮሴፍ የግብጽ ምድር አስተዳዳሪ በመሆኑ ከዓለም ዙሪያ ለሚመጡ ሰዎች ሁሉ እህል እንዲሸጥላቸው ያደርግ ነበር፤ ስለዚህ የዮሴፍ ወንድሞች ወደ እርሱ መጡና ግንባራቸው መሬት እስኪነካ ዝቅ ብለው እጅ ነሡት።
ከኢያሪኮ የመጡት ነቢያት እርሱን ባዩት ጊዜ “በኤልያስ ላይ ዐድሮ የነበረው የመንፈስ ኀይል በኤልሳዕ ላይ አርፏል!” አሉ፤ ወደ እርሱም በመቅረብ ጐንበስ ብለው እጅ ነሡት
እንግዳ ተቀብሎ ማስተናገድን አትርሱ፤ እንደዚህ እንግዶችን እየተቀበሉ በማስተናገድ አንዳንድ ሰዎች ሳያውቁ መላእክትን ተቀብለው አስተናግደዋል።
ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ሰይፍ የያዘ አንድ ጐልማሳ በድንገት በፊቱ ቆሞ ታየው፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ “አንተ የእኛ ወገን ነህ ወይስ የጠላቶቻችን?” አለው።
ለእርስዋም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ እንዲህ አላት፤ “አንቺ መኻን ነሽ፤ ልጆችም የሉሽም፤ ነገር ግን ትፀንሺአለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤
እርስዋም ግንባርዋ መሬት እስኪነካ ድረስ እጅ ነሥታ “እኔ ባዕድ ሆኜ ሳለ ስለ እኔ ታስብ ዘንድ እንዴት በፊትህ ሞገስ ላገኝ ቻልኩ?” አለችው።