ዘፍጥረት 17:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተና ከአንተ በኋላ የሚመጣው ዘርህ የምትጠብቁት ቃል ኪዳን ይህ ነው፤ በመካከላችሁ ያሉት ወንዶች ሁሉ መገረዝ አለባቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተና ከአንተም በኋላ የሚመጣው ዘርህ የምትጠብቁት ኪዳን ይህ ነው፤ በመካከላችሁ ያለ ወንድ ሁሉ ይገረዝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእኔና በአንተ መካከል፥ ከአንተም በኋላ በዘርህ መካከል የምትጠብቁት ቃል ኪዳኔ ይህ ነው፥ በመካከላችሁ ያለ ወንድ ሁሉ ይገረዝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእኔና በአንተ መካከል፥ ከአንተም በኋላ በዘርህ መካከል የምትጠብቋት ቃል ኪዳኔ ይህች ናት፤ ከእናንተ ወንድ ሁሉ ይገረዝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእኔና በአንተ መካከለ ከአንተም በኍላ በዘርህ መካከል የምትጠብቁት ቃል ኪዳኔን ይህ ነው ከእናንተ ወንድ ሁሉ ይገረዝ። |
እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት አብርሃም በዚያኑ ቀን ልጁን እስማኤልን ገረዘው፤ እንዲሁም በቤቱ ውስጥ የተወለዱና ከውጪ የተገዙ ባሪያዎች ሳይቀሩ፥ በቤቱ ያሉትን ወንዶች ሁሉ ገረዘ፤
ሆኖም እነዚህ ሰዎች አብረውን ለመኖርና ከእኛም ጋር አንድ ሕዝብ ለመሆን ፈቃደኞች የሚሆኑት ወንዶች የሆንን ሁሉ እንደ እነርሱ ለመገረዝ የተስማማን እንደ ሆነ ነው።
ነገር ግን ያልተገረዘ ማንም ሰው አይብላ፤ የውጪ አገር ሰው በመካከላችሁ ቢኖርና የእግዚአብሔርን የፋሲካ በዓል ማክበር ቢፈልግ፥ አስቀድማችሁ በቤተሰቡ ያሉትን ወንዶች ሁሉ ግረዙ፤ ከዚያም በኋላ የሀገር ተወላጅ እስራኤላዊ እንደ ሆነ ተቈጥሮ የፋሲካን በዓል ለማክበር ከእናንተ ጋር ይተባበር።
ከዚያ በኋላ ሲፖራ ሮጣ ሄዳ ባልጩት አመጣችና የልጅዋን ሸለፈት ገረዘች፤ የሙሴንም እግር በሸለፈቱ ዳስሳ “በእርግጥ አንተ ለእኔ የደም ሙሽራ ነህ” አለች።
እናንተ የይሁዳ ሕዝብና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሆይ! የልባችሁን ክፋት ገርዛችሁ አእምሮአችሁን በማንጻት ሁለንተናችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ይህን ባታደርጉ ግን በክፉ ሥራችሁ ምክንያት ቊጣዬ እንደ እሳት ይነዳል፤ ቊጣዬም ከነደደ ማንም ሊያጠፋው አይችልም።”
ሙሴ የግዝረትን ሥርዓት ሰጣችሁ፤ ይህም ሥርዓት የተገኘው፤ ከአባቶች ነው እንጂ ከሙሴ አይደለም፤ እናንተም እኮ በሰንበት ሰውን ትገርዛላችሁ።
የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ ስለዚህ አብርሃም ይስሐቅን በወለደ ጊዜ በስምንተኛው ቀን ገረዘው፤ እንዲሁም ይስሐቅ ልጁን ያዕቆብን ገረዘው። ያዕቆብም የነገድ አባቶች የሆኑትን ዐሥራ ሁለቱን ልጆቹን ገረዘ።
እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ በደሙ የኃጢአታቸውን ስርየት እንዲያገኙ ነው፤ እግዚአብሔር ይህን ማድረጉ በትዕግሥቱ የቀድሞውን ኃጢአት እንዳልነበረ በማድረግ የራሱን ትክክለኛ ፍርድ ለመግለጥ ነው።
እንድትገረዙ የሚያስገድዱአችሁ በውጭ መልካም መስለው ለመታየት የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው። ይህን የሚያደርጉትም በክርስቶስ መስቀል ምክንያት ስደት እንዳይደርስባቸው ብለው ነው።
ስለዚህ እናንተ ቀድሞ በትውልዳችሁ አሕዛብ የነበራችሁ፥ አይሁድ በሰው እጅ በመገረዛቸው እየተመኩ እናንተን ያልተገረዙ እያሉ ይሰድቡአችሁ እንደ ነበር አስታውሱ።
አምላክህ እግዚአብሔር ለአንተና ለልጆችህ ታዛዥ ልብ ይሰጣል፤ ስለዚህም እርሱን በፍጹም ልብህ ትወደዋለህ፤ በዚያችም ምድር በሕይወት ትኖራለህ።
እኛ እግዚአብሔርን በመንፈስ የምናመልክና በውጭ በሚታየው ሥርዓት ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ የምንመካ ስለ ሆንን በእውነት ተገርዘናል።
ኢያሱ እነርሱን የገረዘበት ምክንያት ከግብጽ ምድር የወጡት ለወታደርነት ብቃት የነበራቸው ወንዶች ሁሉ በበረሓው ጒዞ ጊዜ ሞተው ስለ ነበረ ነው።