ስለዚህ ሰዎች በቃዴስና በባሬድ መካከል የሚገኘውን የውሃ ጒድጓድ “ብኤር ላሐይ ሮኢ” ብለው ይጠሩታል፤ ትርጒሙም “ሕያው የሆነውና የሚያየኝ አምላኬ ጒድጓድ” ማለት ነው።
ዘፍጥረት 14:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ተመልሰው ወደ ቃዴስ መጡ፤ በዚያን ጊዜ የዚህ ቦታ ስም ዔይንሚሽፖጥ ይባል ነበር። የዐማሌቃውያንንም ምድር ሁሉ ያዙ፤ በሐጸጾን ታማር ይኖሩ የነበሩትን አሞራውያንንም አሸነፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ተመልሰው ዓይንሚስፖጥ ወደተባለው ወደ ቃዴስ መጡ፤ የአማሌቃውያንና በሐሴሶን ታማር ይኖሩ የነበሩትን የአሞራውያንን ግዛት በሙሉ ድል አድርገው ያዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተመልሰውም ቃዴስ ወደተባለች ወደ ዓይንሚስፓጥ መጡ፥ የአማሌቅን አገር ሁሉና ደግሞ በሐሴቦን ታማር የነበረውን አሞራውያንን መቱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተመልሰውም ቃዴስ ወደ ተባለች ወደ ፍርድ ምንጭ መጡ፤ የአማሌቅን አለቆች ሁሉና በአሳሶን ታማር የሚኖሩ አሞራውያንንም ገደሉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተመልሰውም ቃዴስ ወደ ተባለች ወደ ዓይንሚስፓጥ መጡ፤ የአማሌቅን አገር ሁሉና ደግሞ በሐሴሶን ታማር የነበረውን አሞራውያንን መቱ። |
ስለዚህ ሰዎች በቃዴስና በባሬድ መካከል የሚገኘውን የውሃ ጒድጓድ “ብኤር ላሐይ ሮኢ” ብለው ይጠሩታል፤ ትርጒሙም “ሕያው የሆነውና የሚያየኝ አምላኬ ጒድጓድ” ማለት ነው።
የዔሳው ልጅ ኤሊፋዝ ቲመናዕ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ እርስዋ ለኤሊፋዝ ዐማሌቅን ወለደችለት፤ እነዚህም የዔሳው ሚስት የዓዳ የልጅ ልጆች ናቸው።
ሰዎች መጥተው ለንጉሥ ኢዮሣፍጥ “በአንተ ላይ አደጋ ለመጣል እጅግ ብዙ የሆነ ሠራዊት ከሙት ባሕር ባሻገር ካለው ከኤዶም ምድር መጥቶብሃል፤ እነሆ ሐጸጾንታማርን ቀደም ሲል በድል አድራጊነት ይዘዋል” ሲሉ ነገሩት፤ (ሐጸጾንታማር የዔንገዲ ሌላ መጠሪያ ስሙ ነው፤)
ከዔንገዲ ጀምሮ እስከ ዔንዔግላይም ድረስ ዓሣ አጥማጆች ይቆማሉ፤ ያም ቦታ መረቦች የሚዘረጉበት ቦታ ይሆናል፤ በሜዲትራኒያን ባሕር እንደሚገኘው ዐይነት በዚህም ልዩ ልዩ ዓሣ ይገኛል።
የጋድ ደቡባዊ ድንበር ከታማር ከተማ ደቡብ ተነሥቶ በመሪባ ቃዴስ እስከምትገኘው የውሃ ምንጭ ይዘልቃል፤ ከዚያም የግብጽ ወሰን የሆነውን ወንዝ ተከትሎ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ይደርሳል።
በፋራን ምድረ በዳ በቃዴስ ወደነበሩት ወደ ሙሴና አሮን ወደ መላውም የእስራኤል ማኅበር መጡ፤ እነርሱም ያዩትን ነገር ሁሉ አስረዱ፤ ያመጡትንም ፍሬ አሳዩአቸው፤
ዐማሌቃውያንንና ከነዓናውያንን ፊት ለፊት ባያችሁ ጊዜ በጦርነት ትሞታላችሁ፤ እርሱን መከተል እምቢ ስላላችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር አይሆንም።”
ከዚህ በኋላ በለዓም ወደ ዐማሌቅ በመመልከት እንዲህ ሲል ይህን የትንቢት ቃል ተናገረ፦ “ዐማሌቅ ከሁሉ የሚበልጥ ኀያል ሕዝብ ነበረ፤ በመጨረሻ ግን እርሱ ራሱ ለዘለዓለም ይጠፋል።”
“ከዚያም እግዚአብሔር አምላካችን እንዳዘዘን ከሲና ተነሥተን እናንተ ባያችሁት አስቸጋሪ በረሓ በተራራማው በአሞራውያን አገር በኩል አድርገን ወደ ቃዴስ በርኔ መጣን።