ዘፍጥረት 14:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብራምም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በልዑል እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብራም ግን ለሰዶም ንጉሥ እንዲህ አለው፤ “ሰማይንና ምድርን ወደ ፈጠረ ወደ እግዚአብሔር፣ ወደ ልዑል አምላክ እጆቼን አንሥቻለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብራምም የሰዶምን ንጉሥ አለው፦ ሰማይንና ምድርን ወደሚገዛ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጄን ከፍ አድርጌአለሁ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብራምም የሰዶምን ንጉሥ አለው፥ “ሰማይንና ምድርን ወደ ፈጠረ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጄን ከፍ አደርጋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብራምም የስዶምን ንጉሥ አለው፤ ሰማይንና ምድርን ወደ ሚግዛ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጄን ከፍ አድርጌአለሁ፤ |
አብራም 99 ዓመት በሆነው ጊዜ እግዚአብሔር ተገለጠለትና “እኔ ኤልሻዳይ ሁሉን የምችል አምላክ ነኝ፤ ለእኔ በመታዘዝ ዘወትር ትክክል የሆነውን ነገር አድርግ፤
ይኸውም እኔ በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳትመርጥ በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ፤
ዳዊት ወደ ያቤሽ ገለዓድ ሰዎች መልእክተኞችን ልኮ እንዲህ አላቸው፦ “እርሱን በመቅበር ለጌታችሁ ለሳኦል ቸርነትን ስላሳያችሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ።
ኤልሳዕም “በማገለግለው በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ ምንም ነገር አልቀበልም” ሲል መለሰለት። ንዕማንም ስጦታውን እንዲቀበልለት አጥብቆ ቢለምነውም ኤልሳዕ ሊቀበለው አልፈቀደም፤
አንተ ታላቅና ኀያል ነህ፤ በክብር፥ በውበትና በግርማም የተሞላህ ነህ፤ በሰማይና በምድር ያለው ነገር ሁሉ የአንተ ነው፤ አንተ ከሁሉ በላይ ከፍ ያልክና በሁሉም ላይ ሥልጣን ያለህ ንጉሥ ነህ፤
ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ አወርሳቸው ዘንድ በመሐላ ቃል ኪዳን ወደገባሁባት ምድር አመጣችኋለሁ፤ ርስትም አድርጌ አወርሳችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ”
ከፍተኛውና ከሁሉ የላቀው፥ ለዘለዓለም የሚኖር ቅዱሱ እንዲህ ይላል፦ “እኔ በተቀደሰና በከፍተኛ ቦታ፥ እንዲሁም ልባቸው ከተሰበረና መንፈሳቸው ትሑት ከሆኑት ጋር እኖራለሁ፤ ይኸውም ትሑት መንፈሳቸውንና የተሰበረ ልባቸውን ለማደስ ነው።
ቀጭን ሐር ለብሶ ከወንዝ በላይ በኩል የቆመው መልአክ ሁለት እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ በዘለዓለማዊው አምላክ ስም በመማል “ሦስት ዓመት ተኩል ይወስዳል፤ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ የሚደርሰው መከራ ሲያከትም እነዚህ ሁሉ ነገሮች ተፈጻሚነት ያገኛሉ።”
ንጉሡ ናቡከደነፆር እንዲህ አለ፦ “ሰባቱ ዓመቶች ካለፉ በኋላ ቀና ብዬ ወደ ሰማይ ተመለከትኩ፤ አእምሮዬም ተመለሰልኝ፤ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገንኩ፤ ለዘለዓለማዊው አምላክ ክብርና ውዳሴ አቀረብኩ፤ “ግዛቱ ዘለዓለማዊ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፤
ባያትም ጊዜ በሐዘን ልብሱን በመቅደድ “ወዮ ልጄ! ልቤን በሐዘን ሰበርሽው! ለታላቅ ጭንቀትም ዳረግሽኝ፤ ለእግዚአብሔር ቃል ገብቼአለሁና ስለቴን ልመልሰውም አልችልም፤” አለ።