ምድሪቱ ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ተለይተህ ሂድ፤ አንተ ወደ ግራ ብትሄድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ ወይም አንተ ወደ ቀኝ ብትሄድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።”
ዘፍጥረት 13:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አብራም ሎጥን እንዲህ አለው፤ “እኛ ወንድማማች ስለ ሆንን በእኔና በአንተ መካከል እንዲሁም በእኔ እረኞችና በአንተ እረኞች መካከል ጠብ ሊነሣ አይገባም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብራምም ሎጥን እንዲህ አለው፤ “እኛ ወንድማማቾች ነንና፣ በአንተና በእኔ ወይም በእረኞቻችን መካከል ጠብ ሊኖር አይገባም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብራምም ሎጥን አለው፦ እኛ ወንድማማች ነንና በእኔና በአንተ በእረኞቼና በእረኞችህ መካከል ጠብ እንዳይሆን እለምንሃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብራምም ሎጥን አለው፥ “እኛ ወንድማማች ነንና በእኔና በአንተ፥ በእረኞቼና በእረኞችህ መካከል ጠብ አይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብራምም ሎጥን አለው እኛ ወንድማምች ነንና በእኔና በአንተ በእረኞቼና በእረኞችህ መካከል ጠብ እንዳይሆን እለምንሃለሁ። |
ምድሪቱ ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ተለይተህ ሂድ፤ አንተ ወደ ግራ ብትሄድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ ወይም አንተ ወደ ቀኝ ብትሄድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።”
አብራም የወንድሙ ልጅ እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ በቤቱ ተወልደው የጦር ልምምድ ያላቸውን 318 ሰዎች በትጥቅ አደራጅቶ አራቱን ነገሥታት በመከታተል እስከ ዳን ድረስ ሄደ።
‘እኛ ልክ እንደ ቀድሞ አባቶቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ የምንተዳደረው በግ በማርባት ነው’ ብላችሁ መልሱለት። በግ አርቢዎች በግብጻውያን ዘንድ የተናቁ ስለ ሆኑ ይህን በመናገር በጌሴም ምድር ለመኖር ፈቃድ ታገኛላችሁ።”
በማግስቱም ወደዚያው ስፍራ ተመልሶ ሲሄድ ሁለት ዕብራውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አየ፤ በደል የሠራውንም ሰው ተመልክቶ “ወገንህ የሆነውን ዕብራዊ ለምን ትመታዋለህ?” ሲል ጠየቀው።
በማግስቱም ሁለት እስራኤላውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አገኘና ሊገላግላቸው በመፈለግ ‘እናንተ ሰዎች፥ እናንተ ወንድማማች ናችሁ፤ ስለምን ትጣላላችሁ?’ አላቸው።
ለምእመናን ቅንነት የተሞላበት ፍቅር እንዲኖራችሁ ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን አንጽታችኋል፤ ስለዚህ በሙሉ ልባችሁ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።
በቀረውስ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ በመስማማት ኑሩ፤ የሌላውን ሰው ችግር እንደ ራሳችሁ አድርጋችሁ ቊጠሩ፤ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ ደጎችና ትሑቶች ሁኑ።