ደግሞም እግዚአብሔር አብራምን “ይህችን አገር በውርስ ለአንተ እንድሰጥህ ዑር ከምትባለው ከከለዳውያን ምድር ያወጣሁህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ” አለው።
ዘፍጥረት 12:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፤ “አገርህን ትተህ፥ ከዘመዶችህና ከአባትህ ቤተሰብ ተለይተህ፥ እኔ ወደማሳይህ አገር ሂድ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፤ “ከአገርህ ከወገንህ ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም አብራምን አለው፦ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አብራምን አለው፥ “ከሀገርህ፥ ከዘመዶችህም፥ ከአባትህም ቤት ተለይተህ ውጣ፤ እኔ ወደማሳይህም ምድር ሂድ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም አብራምን አለው፤ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ። |
ደግሞም እግዚአብሔር አብራምን “ይህችን አገር በውርስ ለአንተ እንድሰጥህ ዑር ከምትባለው ከከለዳውያን ምድር ያወጣሁህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ” አለው።
ስለዚህ እግዚአብሔር ከአባቴ ቤት ወጥቼ ወደ ባዕድ አገር እንድሄድ ባዘዘኝ ጊዜ ‘በምንሄድበት ቦታ ሁሉ እኅቱ ነኝ ብትዪ ለእኔ ታላቅ ውለታ እንዳደረግሽልኝ እቈጥረዋለሁ’ ብዬአት ነበር።”
ከአባቴ ቤትና ከትውልድ አገሬ አውጥቶ ይህን ምድር ለዘሬ እንደሚሰጥ በመሐላ ቃል የገባልኝ እግዚአብሔር፥ የሰማይ አምላክ ከዚያ ለልጄ ሚስት ማግኘት እንድትችል መልአኩን በፊትህ ይልካል።
የቀድሞ አባቶቼ የጎዛንን፥ የካራንና የሬጼፍን ከተሞች አጥፍተዋል፤ በተላሳር ይኖሩ የነበሩትን የዔደንን ሕዝብ ገድለዋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ከአማልክታቸው አንዳቸው እንኳ ሊያድኑአቸው ችለዋልን?
ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃምና ወደ ወለደቻችሁ ወደ ሣራ ተመልከቱ፤ አብርሃምን በጠራሁት ጊዜ ልጅ አልነበረውም፤ ነገር ግን እኔ ባረክሁት፤ ዘሩንም አበዛሁለት።
“የሰው ልጅ ሆይ! በእስራኤል ምድር በፈራረሱ ከተሞች የሚኖሩ ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ ‘አብርሃም ብቸኛ የሆነ አንድ ሰው ነበረ፤ ምድሪቱ በሞላ ለእርሱ ተሰጠች፤ እኛ ግን እነሆ፥ ብዙዎች ነን፤ ምድሪቱም በእርግጥ በርስትነት ተሰጥታናለች።’
አብርሃም ወጥቶ ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ ምንም እንኳ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም ለመሄድ የታዘዘው በእምነት ነው።