ካህኑ ዕዝራም ቆሞ እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “እነሆ እምነታችሁን አጓድላችሁ ተገኝታችኋል፤ ባዕዳን ሴቶችንም በማግባታችሁ ምክንያት በእስራኤል ላይ የበደልን ዕዳ አምጥታችኋል።
ዕዝራ 9:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ እንዴት እንደገና የአንተን ትእዛዞች ጥሰን ከእነዚህ ዐመፀኞች ሕዝቦች ጋር ጋብቻ እንፈጽማለን? በዚህስ ምክንያት ምንም ቅሬታ ሳታስቀርልን እኛን በቊጣህ አታጠፋንምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ ትእዛዞችህን እንደ ገና ተላልፈን እንዲህ ያለውን አስጸያፊ ድርጊት ከሚፈጽሙ ሕዝቦች ጋራ መጋባት ተገቢ ነውን? አንተስ ቅሬታ እስከማይኖር ወይም አንድም ሰው እስከማይድን ድረስ ተቈጥተህ አታጠፋንምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትእዛዝህን ለማፍረስ፥ ርኩስ ሥራን ከሚሠሩ ከእነዚህም ሕዝቦች ጋር ለመጋባት እንመለሳለንን? አንተስ ትሩፋን የሌለንና የማናመልጥ እስክንሆን ድረስ እንድታጠፋን አትቆጣምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትእዛዝህን እናፈርስ ዘንድ ተመልሰናልና፥ ርኵስ ሥራ ከሚሠሩ ከእነዚህ አሕዛብ ጋርም ተጋብተናልና ከእኛ ከሞት የሚያመልጥ እስከማይኖር ድረስ ፈጽመህ አትቈጣን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ተመልሰን ትእዛዝህን እናፈርስ ዘንድ፥ ርኩስ ሥራን ከሚሠሩ ከእነዚህም አሕዛብ ጋር እንጋባ ዘንድ ይገባናልን? አንተስ ቅሬታ የሌለንና የማናመልጥ እስክንሆን ድረስ እንድታጠፋን አትቈጣንም? |
ካህኑ ዕዝራም ቆሞ እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “እነሆ እምነታችሁን አጓድላችሁ ተገኝታችኋል፤ ባዕዳን ሴቶችንም በማግባታችሁ ምክንያት በእስራኤል ላይ የበደልን ዕዳ አምጥታችኋል።
ለራሳቸውና ለልጆቻቸው ሚስቶች የሚሆኑ ከእነዚያ ወገኖች አግብተዋል፤ አጋብተዋልም፤ ቅዱሱን ዘር ከሌሎች ከአካባቢው አሕዛብ ጋር ቀላቅለዋል፤ በዚህ እምነተ ቢስ በሆነ ተግባር መሪዎቹና ባለ ሥልጣኖቹ ግንባር ቀደም ሆነዋል።”
አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ዐይናችንን አበራህ፤ እነሆ፥ አሁን ደግሞ ለጥቂት ጊዜ በፊትህ ሞገስን አግኝተን ከእኛ ጥቂቶቹ ከባርነት ቀንበር ነጻ ወጥተው በዚህች ቅድስት ምድር በሰላም ይኖሩ ዘንድ ፈቅደሃል፤ ምንም እንኳ በባርነት አገዛዝ ሥር ብንወድቅም እነሆ አዲስ ሕይወት ሰጥተኸናል።
አምላካችን በእኛና በከተማይቱ ላይ ይህን ጥፋት ያመጣው የቀድሞ አባቶቻችሁ ይህን ጥፋት ስላደረጉ አይደለምን? አሁንም እናንተ ሰንበትን ባለማክበራችሁ የእግዚአብሔርን ቊጣ በእስራኤል ላይ ታነሣሣላችሁ።”
በቀድሞ አባቶቻችሁ፥ በይሁዳ ነገሥታትና በሚስቶቻቸው፥ በእናንተ በራሳችሁና በሚስቶቻችሁ አማካይነት በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ የተፈጸመውን ክፉ ሥራ ሁሉ ረስታችሁታልን?
እኔ ከእናንተ ጋራ ስለ ሆንኩ አገልጋዮቼ እስራኤላውያን ሆይ! እናንተ አትፍሩ፤ እናንተ በሀገራቸው እንድትበታተኑ ያደረግኹባቸውን ሕዝቦች ሁሉ አጠፋለሁ፤ እናንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋችሁም፤ ሆኖም ለማረም እቀጣችኋለሁ፤ ሳልቀጣችሁ ግን አላልፍም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
“ነገር ግን ጥቂቶቻችሁ እንድትተርፉ አደርጋለሁ፤ ጥቃቶቻችሁ ወደ ሌሎች ሕዝቦች በመሄድ ከጦርነት አምልጣችሁ በተለያዩ አገሮች ትበተናላችሁ።
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሰውየውን በቤተ መቅደስ አገኘውና “እነሆ፥ አሁን ድነሃል፤ ከዚህ የባሰ ነገር እንዳይደርስብህ ከእንግዲህ ወዲህ ኃጢአት አትሥራ” አለው።
እንግዲህ ተወኝ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ማንም ሊያስታውሳቸው በማይችል ሁኔታ ልደምስሳቸው፤ ከዚያም በኋላ አንተን ከእነርሱ ይበልጥ ኀይልና ብዛት ላለው ሕዝብ አባት አደርግሃለሁ።’
እናንተ በዚች ምድር ከሚኖሩ ሕዝብ ጋር ምንም ዐይነት ቃል ኪዳን አታድርጉ፤ መሠዊያዎቻቸውንም አፍርሱ፤’ እናንተ ግን አልታዘዛችሁኝም፤ ይህንስ ያደረጋችኹት ለምንድን ነው?