ዕዝራ 9:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ትእዛዝህን ለማፍረስ፥ ርኩስ ሥራን ከሚሠሩ ከእነዚህም ሕዝቦች ጋር ለመጋባት እንመለሳለንን? አንተስ ትሩፋን የሌለንና የማናመልጥ እስክንሆን ድረስ እንድታጠፋን አትቆጣምን? Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ታዲያ ትእዛዞችህን እንደ ገና ተላልፈን እንዲህ ያለውን አስጸያፊ ድርጊት ከሚፈጽሙ ሕዝቦች ጋራ መጋባት ተገቢ ነውን? አንተስ ቅሬታ እስከማይኖር ወይም አንድም ሰው እስከማይድን ድረስ ተቈጥተህ አታጠፋንምን? Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ታዲያ እንዴት እንደገና የአንተን ትእዛዞች ጥሰን ከእነዚህ ዐመፀኞች ሕዝቦች ጋር ጋብቻ እንፈጽማለን? በዚህስ ምክንያት ምንም ቅሬታ ሳታስቀርልን እኛን በቊጣህ አታጠፋንምን? Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ትእዛዝህን እናፈርስ ዘንድ ተመልሰናልና፥ ርኵስ ሥራ ከሚሠሩ ከእነዚህ አሕዛብ ጋርም ተጋብተናልና ከእኛ ከሞት የሚያመልጥ እስከማይኖር ድረስ ፈጽመህ አትቈጣን። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 በውኑ ተመልሰን ትእዛዝህን እናፈርስ ዘንድ፥ ርኩስ ሥራን ከሚሠሩ ከእነዚህም አሕዛብ ጋር እንጋባ ዘንድ ይገባናልን? አንተስ ቅሬታ የሌለንና የማናመልጥ እስክንሆን ድረስ እንድታጠፋን አትቈጣንም? Ver Capítulo |