ዕዝራ 8:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ታላቅ ኀይል ከእኛ ጋር ስለ ነበረ እነርሱ በቂ ችሎታ ያለውን፥ የማሕሊ ጐሣ የሆነውን ሼሬብያ ተብሎ የሚጠራውን ሌዋዊ ላኩልን፤ እርሱም ዐሥራ ስምንቱን ወንዶች ልጆቹንና ወንድሞቹን አስከትሎ ወደ እኛ መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካሚቱ የአምላካችን እጅ በእኛ ላይ ስለ ነበረች፣ ከሞሖሊ ዘሮች የእስራኤል ልጅ የሌዊ ልጅ የሆነውን ሰራብያ ተብሎ የሚጠራውን አስተዋይ ሰው፣ ከርሱም ጋራ ዐሥራ ስምንት የሚሆኑ ወንዶች ልጆቹንና ወንድሞቹን አመጡልን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአምላካችን መልካም እጅ በላያችን ላይ ስለ ነበረች፥ የእስራኤል ልጅ የሌዊ ልጅ ከሆነው ከማሕሊ ልጆች ወገን የነበረውን አስተዋይ ሰው ሼሬብያን፥ ከእርሱም ጋር ዐሥራ ስምንት ልጆቹንና ወንድሞቹን አመጡልን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በላያችንም መልካም በሆነው በአምላካችን እጅ ከእስራኤል ልጅ ከሌዊ ልጅ ከሞሐሊ ልጆች ወገን የነበረውን አስተዋይ ሰው ሰራብያን፥ ከእርሱም ጋር ዐሥራ ስምንቱን ልጆቹንና ወንድሞቹን አመጡልን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በላያችንም መልካም በሆነው በአምላካችን እጅ ከእስራኤል ልጅ ከሌዊ ልጅ ከሞሖሊ ልጆች ወገን የነበረውን አስተዋይ ሰው ሰራብያን፥ ከእርሱም ጋር አሥራ ስምንቱን ልጆቹንና ወንድሞቹን አመጡልን። |
ሕዝቅያስም ለእግዚአብሔር የተደረገውን የአምልኮ ሥነ ሥርዓት በመምራት ከፍ ያለ ችሎታ ስላሳዩ ሌዋውያኑን አመሰገነ። ለቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር ሰባት ቀን የኅብረት መሥዋዕት አቅርበው ከበሉ በኋላ፥
በእግዚአብሔርም ፈቃድ በንጉሠ ነገሥቱና በአማካሪዎቹ፥ በባለሥልጣኖቹም ሁሉ ዘንድ መወደድን አግኝቻለሁ፤ የአምላኬ የእግዚአብሔር ኀይል ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ከእስራኤል የጐሣ መሪዎች ብዙዎቹ ከእኔ ጋር ተባብረው ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ በማግባባት ለማስተማር አብቅቶኛል።”
ይህ ዕዝራ ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ሕግ ሊቅ ነበር፤ የእግዚአብሔር ኀይል ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ ንጉሡ የጠየቀውን ነገር ሁሉ ሰጠው።
የእግዚአብሔር ታላቅ ኀይል በእርሱ ላይ ስለ ነበረ ከባቢሎን በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ተነሥቶ ኢየሩሳሌም በአምስተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ደረሰ።
ስለዚህም ኤሊዔዘር፥ አሪኤል፥ ሸማዕያ፥ ኤልናታን፥ ያሪብ፥ ኤልናታን፥ ናታን፥ ዘካርያስና መሹላም ተብለው ወደሚጠሩ ዘጠኝ መሪዎች፥ እንዲሁም ዮያሪብና ኤልናታን ተብለው ወደሚጠሩ ሁለት መምህራን ላክሁባቸው፤
ከዚህ በፊት ለንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ ባስረዳሁት ጊዜ “አምላካችን እግዚአብሔር በእርሱ የሚታመኑትን ሁሉ ይባርካል፤ እርሱን የሚተዉትን ግን በብርቱ ይቀጣቸዋል” በማለት ገልጬለት ስለ ነበረ በመንገድ ከሚገጥሙን ጠላቶቻችን እንዲጠብቁን ወታደሮችንና ፈረሰኞችን ይሰጠን ዘንድ ንጉሡን ጠይቄው ቢሆን ኖሮ ባፈርኩ ነበር።
ሌዋውያኑ በሐሻብያ፥ በሼሬብያ፥ በኢያሱ፥ በቢኑይና በቃድሚኤል መሪነት በሁለት ቡድኖች ተከፈሉ። ሁለቱም ቡድኖች የእግዚአብሔር ሰው የሆነ ንጉሥ ዳዊት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እየተቀባበሉ የምስጋና መዝሙር በማቅረብ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።
እንዲሁም አሳፍ የተባለው፥ የመንግሥት ደን ጠባቂ የሆነው፥ ለቤተ መቅደሱ ቅጽር በርና ለከተማይቱ ቅጽር በሮች ሁሉ እኔም ለማርፍበት ቤት ጭምር መጠበቂያዎች ማሠሪያ የሚሆን የጥድና የዝግባ እንጨት ለመቊረጥ እንዲፈቅድልኝ የሚያዝ ደብዳቤ እንዲሰጠኝም ጠየቅሁ፤ እግዚአብሔርም በቸርነቱ ስለ ረዳኝ፥ ንጉሠ ነገሥቱ የጠየቅሁትን ነገር ሁሉ ሰጠኝ።
ከዚህ በኋላ ተነሥተው ባሉበት ስፍራ ቆሙ፤ ከዚህ ቀጥሎ ስማቸው የተዘረዘረ ሌዋውያንም የሕጉን መጽሐፍ ትርጒም ለሕዝቡ አብራሩላቸው፤ እነርሱም ኢያሱ፥ ባኒ፥ ሼሬብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሻበታይ፥ ሆዲያ፥ መዕሤያ፥ ቀሊጣ፥ ዐዛርያስ፥ ዮዛባድ፥ ሐናንና ፐላያ ነበሩ።
ጥበብና ማስተዋልን በተመለከቱ ጉዳዮች ንጉሡ በሚጠይቃቸው ነገሮች በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት ከሚገኙ ጠንቋዮችና አስማተኞች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ብልጫ ያላቸው ሆነው አገኛቸው።