Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 7:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በእግዚአብሔርም ፈቃድ በንጉሠ ነገሥቱና በአማካሪዎቹ፥ በባለሥልጣኖቹም ሁሉ ዘንድ መወደድን አግኝቻለሁ፤ የአምላኬ የእግዚአብሔር ኀይል ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ከእስራኤል የጐሣ መሪዎች ብዙዎቹ ከእኔ ጋር ተባብረው ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ በማግባባት ለማስተማር አብቅቶኛል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 እንዲሁም በንጉሡ፣ በአማካሪዎቹና በኀያላን ሹሞቹ ፊት ሁሉ ሞገስን የሰጠኝ አምላክ የተመሰገነ ይሁን። የአምላኬ የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ስለ ነበረች፣ ዐብረውኝ እንዲሄዱ ከእስራኤል መካከል የታወቁ ሰዎችን ለመሰብሰብ ብርታት አገኘሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 በንጉሡ፥ በአማካሪዎቹና በኃያላን ባለሥልጣኖቹም ሁሉ ፊት ፅኑ ፍቅሩን በእኔ ላይ ዘረጋ፤ እኔም በላዬ ባለችው በእግዚአብሔር እጅ ራሴን አበረታሁ፥ ከእኔም ጋር እንዲወጡ ከእስራኤል አለቆችን ሰበሰብሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 በን​ጉሡ ፊት በሚ​መ​ክ​ሩ​ትም፥ በኀ​ያ​ላ​ኑም፥ በን​ጉሡ አለ​ቆች ሁሉ ፊት በእኔ ላይ ምሕ​ረ​ቱን ላከ። እኔም በእኔ ላይ ባለ​ችው በአ​ም​ላኬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በረ​ታሁ፤ ከእ​ኔም ጋራ ይወጡ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆ​ቹን ሰበ​ሰ​ብሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 7:28
15 Referencias Cruzadas  

ሰውየውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ከእግዚአብሔርም ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃል፤ ስለዚህ ስምህ ‘እስራኤል’ ይባላል” አለው።


ብንያምንና ሌላውንም ወንድማችሁን መልሶ እንዲሰጣችሁ ሁሉን የሚችል አምላክ የዚያን ሰው ልብ ያራራላችሁ። እኔ በበኩሌ ልጆቼን ካጣሁ፥ ባዶ እጄን መቅረቴ ነው።”


ነገር ግን የአይሁድ መሪዎችን እግዚአብሔር ይጠብቃቸው ስለ ነበር ለፋርስ ባለ ሥልጣኖች ለዳርዮስ መልእክት ጽፈው መልስ እስከሚያገኙ ድረስ ሥራውን ከመቀጠል አልከለከሉአቸውም።


ከዚህም ጋር እኔ ራሴ ከሰባቱ አማካሪዎቼ ጋር በአንድነት ያስተላለፍነውን ውሳኔ ለአንተ የተሰጠው የአምላክህ ሕግ በተግባር መፈጸሙን እየተመለከትህ፥ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያለውን ሁኔታ እንድትመረምር ልኬሃለሁ።


ይህ ዕዝራ ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ሕግ ሊቅ ነበር፤ የእግዚአብሔር ኀይል ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ ንጉሡ የጠየቀውን ነገር ሁሉ ሰጠው።


የእግዚአብሔር ታላቅ ኀይል በእርሱ ላይ ስለ ነበረ ከባቢሎን በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ተነሥቶ ኢየሩሳሌም በአምስተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ደረሰ።


በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት ከእኔ ጋር ከባቢሎን የተመለሱት የቤተሰብ አለቆች በየትውልዳቸው እንደሚከተለው ነው፦


እኔ ዕዝራ ወደ አሀዋ በሚፈሰው ወንዝ አጠገብ መላውን ጉባኤ ሰበሰብኩ፤ በዚያም ሰፍረን ለሦስት ቀኖች ቈየን፤ በዚያም ጉባኤ ውስጥ ከካህናት በቀር ሌዋውያን አለመኖራቸውን ተገነዘብኩ፤


የእግዚአብሔር ታላቅ ኀይል ከእኛ ጋር ስለ ነበረ እነርሱ በቂ ችሎታ ያለውን፥ የማሕሊ ጐሣ የሆነውን ሼሬብያ ተብሎ የሚጠራውን ሌዋዊ ላኩልን፤ እርሱም ዐሥራ ስምንቱን ወንዶች ልጆቹንና ወንድሞቹን አስከትሎ ወደ እኛ መጣ።


እኛ ባርያዎች ነበርን፤ አንተ ግን ባርያዎች ሆነን እንድንቀር አልተውከንም፤ አንተ የፋርስ ነገሥታት እንዲራሩልንና በሕይወት ነጻ ወጥተን ቀደም ሲል ፈርሶ የነበረውን ቤተ መቅደስህን እንደገና መልሰን እንድንሠራ፥ እዚህም በይሁዳና በኢየሩሳሌም በሰላም እንድንኖር ፈቀድክልን።


እነሆ፥ አሁንም የእኔን ጸሎት ስማ፤ አንተን ማክበር የሚወዱትን የሌሎችንም አገልጋዮችህን ጸሎት አድምጥ፤ ዛሬ ልሠራው ያቀድኩት ይሳካልኝ ዘንድ የንጉሠ ነገሥቱን ልብ በማራራት እርዳኝ።” እነሆ፥ እኔ በዚህ ጊዜ የንጉሠ ነገሥቱ ወይን ጠጅ አሳላፊ ነበርኩ።


እንዲሁም አሳፍ የተባለው፥ የመንግሥት ደን ጠባቂ የሆነው፥ ለቤተ መቅደሱ ቅጽር በርና ለከተማይቱ ቅጽር በሮች ሁሉ እኔም ለማርፍበት ቤት ጭምር መጠበቂያዎች ማሠሪያ የሚሆን የጥድና የዝግባ እንጨት ለመቊረጥ እንዲፈቅድልኝ የሚያዝ ደብዳቤ እንዲሰጠኝም ጠየቅሁ፤ እግዚአብሔርም በቸርነቱ ስለ ረዳኝ፥ ንጉሠ ነገሥቱ የጠየቅሁትን ነገር ሁሉ ሰጠኝ።


የሚራራለት ሰው ከቶ አይኑር፤ ድኻ ዐደግ ልጆቹን የሚንከባከባቸው ሰው አይገኝ።


ለነነዌም ሕዝብ እንዲህ ሲል ዐዋጅ አስነገረ፥ “ከንጉሡና ከመኳንንቱ በተላለፈው ትእዛዝ መሠረት፥ ማንም ሰው ወይም እንስሳ፥ የከብትም ሆነ የበግ መንጋ አንዳች ምግብ አይቅመሱ፤ ውሃም አይጠጡ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos