ዕዝራ 7:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 በንጉሡ፥ በአማካሪዎቹና በኃያላን ባለሥልጣኖቹም ሁሉ ፊት ፅኑ ፍቅሩን በእኔ ላይ ዘረጋ፤ እኔም በላዬ ባለችው በእግዚአብሔር እጅ ራሴን አበረታሁ፥ ከእኔም ጋር እንዲወጡ ከእስራኤል አለቆችን ሰበሰብሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም28 እንዲሁም በንጉሡ፣ በአማካሪዎቹና በኀያላን ሹሞቹ ፊት ሁሉ ሞገስን የሰጠኝ አምላክ የተመሰገነ ይሁን። የአምላኬ የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ስለ ነበረች፣ ዐብረውኝ እንዲሄዱ ከእስራኤል መካከል የታወቁ ሰዎችን ለመሰብሰብ ብርታት አገኘሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 በእግዚአብሔርም ፈቃድ በንጉሠ ነገሥቱና በአማካሪዎቹ፥ በባለሥልጣኖቹም ሁሉ ዘንድ መወደድን አግኝቻለሁ፤ የአምላኬ የእግዚአብሔር ኀይል ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ከእስራኤል የጐሣ መሪዎች ብዙዎቹ ከእኔ ጋር ተባብረው ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ በማግባባት ለማስተማር አብቅቶኛል።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 በንጉሡ ፊት በሚመክሩትም፥ በኀያላኑም፥ በንጉሡ አለቆች ሁሉ ፊት በእኔ ላይ ምሕረቱን ላከ። እኔም በእኔ ላይ ባለችው በአምላኬ በእግዚአብሔር እጅ በረታሁ፤ ከእኔም ጋራ ይወጡ ዘንድ ከእስራኤል አለቆቹን ሰበሰብሁ። Ver Capítulo |