1 ዜና መዋዕል 6:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቢሹዓን ወለደ፤ አቢሹዓ ቡቂን ወለደ፤ Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቢሱን ወለደ፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቢሱን ወለደ፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስም አቢሱን ወለደ፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቢሱን ወለደ፤ Ver Capítulo |
ከፊንሐስ ጐሣ ጌርሾም፥ ከኢታማር ጐሣ ዳንኤል፥ ከዳዊት ጐሣ የሸካንያ ልጅ ሐጡሽ፥ ከፓርዖሽ ጐሣ ዘካርያስ ሲሆን፥ ከእርሱ ቤተሰብ ወገን የሆኑ አንድ መቶ ኀምሳ ወንዶች ተመዝግበዋል፤ ከፓሐትሞአብ ጐሣ የዘራሕያ ልጅ ኤልየሆዔናይ ከሁለት መቶ ወንዶች ጋር፥ ከዛቱ ጐሣ የያሐዚኤል ልጅ ሸካንያ ከሦስት መቶ ወንዶች ጋር፥ ከዓዲን ጐሣ የዮናታን ልጅ ዔቤድ ከኀምሳ ወንዶች ጋር፥ ከዔላም ጐሣ የዐታልያ ልጅ የሻዕያ ከሰባ ወንዶች ጋር፥ ከሸፋጥያ ጐሣ የሚካኤል ልጅ ዘባድያ ከሰማንያ ወንዶች ጋር፥ ከኢዮአብ ጐሣ የየሒኤል ልጅ አብድዩ ከሁለት መቶ ዐሥራ ስምንት ወንዶች ጋር፥ ከባኒ ጐሣ የዮሲፍያ ልጅ ሸሎሚት ከአንድ መቶ ሥልሳ ወንዶች ጋር፥ ከቤባይ ጐሣ የቤባይ ልጅ ዘካርያስ ከኻያ ስምንት ወንዶች ጋር፥ ከዓዝጋድ ጐሣ የሃቃጣን ልጅ ዮሐናን ከአንድ መቶ ዐሥር ወንዶች ጋር፥ ከአዶኒቃም ጐሣ ኤሊፌሌጥ፥ ይዒኤልና ሸማዕያ ከስድሳ ወንዶች ጋር፥ እነርሱም ዘግየት ብለው ተመልሰዋል፤ ከቢግዋይ ጐሣ ዑታይና ዛኩር ከሰባ ወንዶች ጋር።