አንተ የሰውን ሁሉ ልብ ፈትነህ፥ ታማኝ በሆነ ሕዝብ እንደምትደሰት ዐውቃለሁ፤ ስለዚህም እኔ ይህን ሁሉ በፈቃዴ ለአንተ የሰጠሁት፥ በታማኝነትና በቅንነት ነው፤ ደግሞም እዚህ የተሰበሰበው ሕዝብህ ለአንተ ስጦታ በማቅረቡ፥ እጅግ መደሰቱን ተገንዝቤአለሁ፤
ዕዝራ 7:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም ሁሉ ጋር አንተ ራስህ ከባቢሎን ምድር የሰበሰብከውን ወርቅና ብር፥ የእስራኤል ሕዝብና ካህናታቸውም ጭምር በኢየሩሳሌም በተሠራው የአምላካቸው ቤተ መቅደስ እንዲቀርብላቸው የሚፈልጉትን መባ ሁሉ ይዘህ ሂድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ከመላው ባቢሎን አውራጃ የምታገኘውን ብርና ወርቅ በሙሉ፣ ሕዝቡና ካህናቱም በኢየሩሳሌም ላለው ለአምላካቸው ቤተ መቅደስ በፈቃዳቸው የሚሰጡትን መባ ሁሉ ይዘህ ሂድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በባቢሎንም አውራጃ ሁሉ የምታገኘውን ብርና ወርቅ በሙሉ፥ ሕዝቡና ካህናቱም በኢየሩሳሌም ላለው ለአምላካቸው ቤት በፈቃዳቸው የሚሰጡትን ይዘህ ሂድ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በባቢሎንም አውራጃ ሁሉ የምታገኘውን ብርና ወርቅ ሁሉ፥ ሕዝቡና ካህናቱም በኢየሩሳሌም ላለው ለአምላካቸው ቤት በፈቃዳቸው የሚያቀርቡትን ትወስድ ዘንድ አዝዘዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በባቢሎንም አውራጃ ሁሉ የምታገኘውን ብርና ወርቅ ሁሉ፥ ሕዝቡና ካህናቱም በኢየሩሳሌም ላለው ለአምላካቸው ቤት በፈቃዳቸው የሚያቀርቡትን ትወስድ ዘንድ በንጉሡና በሰባቱ አማካሪዎች ተልከሃልና |
አንተ የሰውን ሁሉ ልብ ፈትነህ፥ ታማኝ በሆነ ሕዝብ እንደምትደሰት ዐውቃለሁ፤ ስለዚህም እኔ ይህን ሁሉ በፈቃዴ ለአንተ የሰጠሁት፥ በታማኝነትና በቅንነት ነው፤ ደግሞም እዚህ የተሰበሰበው ሕዝብህ ለአንተ ስጦታ በማቅረቡ፥ እጅግ መደሰቱን ተገንዝቤአለሁ፤
ሕዝቡ በፈቃዳቸውና በሙሉ ልብ ሁሉ ለእግዚአብሔር ሰጡ፤ እጅግ ብዙ ሀብት ገቢ በመሆኑም ደስ አላቸው፤ ንጉሥ ዳዊትም ከመጠን በላይ ደስ ተሰኘ።
የቤተ መቅደሱ የምሥራቃዊ በር ዘብ ጠባቂዎች አለቃ ለነበረው ለሌዋዊው ዩምና ልጅ ለቆሬ ደግሞ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን የበጎ ፈቃድ ስጦታዎች ሁሉ የመቀበልና የማከፋፈል ኀላፊነት ተሰጠው።
‘ሕዝቤን ከግብጽ ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በስሜ ቤተ መቅደስ የሚሠራበት ስፍራ ከመላው የእስራኤል ምድር አንድም ከተማ፥ እንዲሁም ሕዝቤን እስራኤልን የሚመራ ማንንም ሰው አልመረጥኩም ነበር፤
እነዚህ ከሞት የተረፉት ሰዎች በሚመለሱበት ጊዜ በአካባቢአቸው የሚኖሩ ሰዎች ብርና ወርቅ፥ ዕቃና የጭነት ከብቶች ይርዱአቸው፤ ይህም በኢየሩሳሌም ለሚገኘው ቤተ መቅደስ በፈቃዳቸው ከሚሰጡት መባ ሌላ ነው።”
ጐረቤቶቻቸውም ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ዕቃዎችን፥ ቈሳቊሶችንና ከብቶችን፥ ሌሎችንም ጠቃሚ የሆኑ ስጦታዎችና በቤተ መቅደስ መባ ሆኖ የሚቀርብ ሌላም ነገር በመለገሥ ረዱአቸው።
ስለዚህ እግዚአብሔር የሚወደው በደስታ የሚሰጠውን ሰው ስለ ሆነ እያንዳንዱ ለመስጠት የፈለገውን በልቡ ፈቅዶ በደስታ ይስጥ እንጂ እያመነታ ወይም በግዴታ አይስጥ።