Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕዝራ 7:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በባ​ቢ​ሎ​ንም አው​ራጃ ሁሉ የም​ታ​ገ​ኘ​ውን ብርና ወርቅ ሁሉ፥ ሕዝ​ቡና ካህ​ና​ቱም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላለው ለአ​ም​ላ​ካ​ቸው ቤት በፈ​ቃ​ዳ​ቸው የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡ​ትን ትወ​ስድ ዘንድ አዝ​ዘ​ዋል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እንዲሁም ከመላው ባቢሎን አውራጃ የምታገኘውን ብርና ወርቅ በሙሉ፣ ሕዝቡና ካህናቱም በኢየሩሳሌም ላለው ለአምላካቸው ቤተ መቅደስ በፈቃዳቸው የሚሰጡትን መባ ሁሉ ይዘህ ሂድ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በባቢሎንም አውራጃ ሁሉ የምታገኘውን ብርና ወርቅ በሙሉ፥ ሕዝቡና ካህናቱም በኢየሩሳሌም ላለው ለአምላካቸው ቤት በፈቃዳቸው የሚሰጡትን ይዘህ ሂድ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚህም ሁሉ ጋር አንተ ራስህ ከባቢሎን ምድር የሰበሰብከውን ወርቅና ብር፥ የእስራኤል ሕዝብና ካህናታቸውም ጭምር በኢየሩሳሌም በተሠራው የአምላካቸው ቤተ መቅደስ እንዲቀርብላቸው የሚፈልጉትን መባ ሁሉ ይዘህ ሂድ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በባቢሎንም አውራጃ ሁሉ የምታገኘውን ብርና ወርቅ ሁሉ፥ ሕዝቡና ካህናቱም በኢየሩሳሌም ላለው ለአምላካቸው ቤት በፈቃዳቸው የሚያቀርቡትን ትወስድ ዘንድ በንጉሡና በሰባቱ አማካሪዎች ተልከሃልና

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 7:16
13 Referencias Cruzadas  

የአ​ባ​ቶ​ችም ቤቶች አለ​ቆች፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አለ​ቆች፥ ሻለ​ቆ​ችም፥ የመቶ አለ​ቆ​ችም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሥራ የተ​ሾ​ሙና የን​ጉሡ ግን​በ​ኞች በፈ​ቃ​ዳ​ቸው አቀ​ረቡ።


በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ያሉ ሁሉ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ካቀ​ረ​ቡት ሁሉ ሌላ በብር ዕቃና በወ​ርቅ፥ በገ​ን​ዘ​ቦ​ችና በእ​ን​ስ​ሶች፥ በሌ​ላም ስጦታ ይረ​ዷ​ቸው ነበር።


በስ​ደት በሚ​ኖ​ር​ባ​ቸው ከተ​ሞች ሁሉ ለቀ​ረው ሰው ሁሉ የሀ​ገሩ ሰዎች በብ​ርና በወ​ርቅ፥ በዕ​ቃም፥ በእ​ን​ስ​ሳም ይር​ዱት፤ ይህም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላለው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ሌላ ይሁን።”


ሕዝ​ቡም ፈቅ​ደው ሰጥ​ተ​ዋ​ልና፥ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃ​ዳ​ቸው አቅ​ር​በ​ዋ​ልና ደስ አላ​ቸው፤ ንጉ​ሡም ዳዊት ደግሞ ታላቅ ደስታ ደስ አለው።


ሁሉ ልቡ እንደ ወደደ ያድ​ርግ፤ በደ​ስታ ይስጡ እንጂ በግድ አይ​ሆ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በደ​ስታ የሚ​ሰ​ጠ​ውን ይወ​ዳ​ልና።


ፈቃድ ካለም፥ ሰው በሚ​ቻ​ለው መጠን ቢሰጥ ይመ​ሰ​ገ​ናል፤ በማ​ይ​ቻ​ለ​ውም መጠን አይ​ደ​ለም።


አም​ላኬ ሆይ፥ ልብን እን​ደ​ም​ት​መ​ረ​ምር፥ ጽድ​ቅ​ንም እን​ደ​ም​ት​ወ​ድድ አው​ቃ​ለሁ፤ እኔም በልቤ ቅን​ነ​ትና በፈ​ቃዴ ይህን ሁሉ አቅ​ር​ቤ​አ​ለሁ፤ አሁ​ንም በዚህ ያለው ሕዝ​ብህ በፈ​ቃዱ እን​ዳ​ቀ​ረ​በ​ልህ በደ​ስታ አይ​ቻ​ለሁ።


እኔም ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ኖ​ር​በት ዝግ​ጁና ቅዱስ ቤት ለስሙ ሠራሁ” አለ።


እርሱ፦ ሕዝ​ቤን ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ሁ​በት ጊዜ ጀምሮ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ በዚያ ለስሜ ቤት ይሠ​ራ​በት ዘንድ ከተ​ማን አል​መ​ረ​ጥ​ሁም። በሕ​ዝቤ እስ​ራ​ኤል ላይም ይነ​ግሥ ዘንድ ሰውን አል​መ​ረ​ጥ​ሁም።


ነገር ግን ስሜ በዚያ እን​ዲ​ጠ​ራ​ባት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን መር​ጫ​ለሁ። በሕ​ዝ​ቤም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ እን​ዲ​ሆን ዳዊ​ትን መር​ጫ​ለሁ ብሎ​አል።


የሌ​ዋ​ዊ​ውም የይ​ም​ላእ ልጅ የም​ሥ​ራቁ ደጅ በረኛ ቆሬ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መባና የተ​ቀ​ደ​ሱ​ትን ነገ​ሮች እን​ዲ​ያ​ካ​ፍል ሕዝቡ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ቀ​ረ​ቡት ላይ ተሾመ።


ርስት ምድ​ራ​ቸ​ውን ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፥ ለባ​ሪ​ያው ለእ​ስ​ራ​ኤል ርስት አድ​ርጎ የሰጠ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios