እንግዲህ አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ አገልግሉ፤ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦትና እግዚአብሔርን ለማምለክ መገልገያ የሆኑትን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ አምጥታችሁ በውስጡ ማኖር ትችሉ ዘንድ ቤተ መቅደሱን ለክብሩ መሥራት ጀምሩ።”
ዘፀአት 9:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀሩት ግን እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል ችላ በማለት አገልጋዮቻቸውንና እንስሶቻቸውን በሜዳ ተዉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርን ቃል ችላ ያሉት ግን ባሮቻቸውንና ከብቶቻቸውን በመስክ ላይ እንደ ነበሩ ተዉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታንም ቃል በልቡ ያላስቀመጠ አገልጋዮቹንና ከብቶቹን በሜዳ ተወ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርን ቃል በልቡ ያላሰበ ግን ከብቶቹን በሜዳ ተወ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርንም ቃል ያላሰበ ባሪያዎቹንና ከብቶቹን በሜዳ ተወ። |
እንግዲህ አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ አገልግሉ፤ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦትና እግዚአብሔርን ለማምለክ መገልገያ የሆኑትን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ አምጥታችሁ በውስጡ ማኖር ትችሉ ዘንድ ቤተ መቅደሱን ለክብሩ መሥራት ጀምሩ።”
ከንጉሡ ባለሟሎች አንዳንዶቹ እግዚአብሔር ስለ ተናገረው ነገር በፍርሃት ተጨነቁ፤ ስለዚህም አገልጋዮቻቸውና እንስሶቻቸው ወደ ቤት ተሰብስበው እንዲጠለሉ አደረጉ።
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፤ በረዶም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ይዘንባል፤ ሕዝቡን፥ እንስሶቹ በእርሻ ያለውን ተክል ሁሉ ይመታል” አለው።
ሰውየውም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! እዚህ ድረስ እንድትመጣ የተደረገበት ምክንያት እኔ የማሳይህን ሁሉ እንድትረዳ ስለ ሆነ ልብ ብለህ ተመልከት፤ በጥንቃቄም ስማ፤ የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ሕዝብ ንገራቸው።”
ደግሞም እንዲህ አለኝ፦ “ዳንኤል ሆይ! አትፍራ! ማስተዋልን ለማግኘት ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ለማዋረድ ከወሰንክበት ከመጀመሪያው ቀን አንሥቶ ጸሎትህ ተሰምቶአል፤ እኔም ተልኬ ወደ አንተ የመጣሁት ጸሎትህ መልስ ከማግኘቱ የተነሣ ነው።
እርስዋም ለመሞት በምታጣጥርበት ጊዜ በማዋለድ የምትረዳት ሴት “አይዞሽ በርቺ! ወንድ ልጅ ወልደሻል!” አለቻት፤ ነገር ግን አዳምጣ መልስ አልሰጠቻትም፤ አላተኰረችበትምም።