ዘፀአት 8:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም አሮን በግብጽ ውሃ ሁሉ ላይ በትሩን ዘረጋ፤ ጓጒንቸሮችም ወጥተው ምድሪቱን አለበሱአት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮንም በግብጽ ውሆች ላይ እጁን ዘረጋ፤ ጓጕንቸሮችም ወጥተው ምድሪቱን ሸፈኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ “ነገ” አለ። ሙሴም እንዲህ አለው፦ “ጌታ አምላካችንን የሚመስል እንደሌለ እንድታውቅ እንደ ቃልህ ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንም በግብፅ ውኆች ላይ እጁን ዘረጋ፤ ጓጕንቸሮቹም ወጡ፤ የግብፅንም ሀገር ሸፈኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንም በግብፅ ውኆች ላይ እጁን ዘረጋ፤ ጓጕንቸሮቹም ወጡ፤ የግብፅንም አገር ሸፈኑ። |
“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! በሰማይም ሆነ በምድር ሁሉ እንደ አንተ ያለ አምላክ ከቶ የለም፤ አንተ ከሕዝብህ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን ትጠብቃለህ፤ በፍጹም ልባቸው በመንገድህ ለሚሄዱ ዘለዓለማዊ ፍቅርህን ትገልጥላቸዋለህ።
እንዲሁም እነዚህን ተአምራት ባደረግሁ ጊዜ ግብጻውያንን እንዴት እንደቀጣሁ ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ መንገር ትችሉ ዘንድ ነው፤ በዚህም ዐይነት ሁላችሁም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”
“አምላክ ሆይ፥ ከአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅድስናስ እንደ አንተ ያለ ባለግርማ ማን ነው? አንተ ያደረግሃቸውን ተአምራትና አስገራሚ ሥራዎች ሊያደርግ የሚችልስ ማን አለ?
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አሮን በትሩን ወስዶ በግብጽ ምድር በሚገኙት ወንዞች፥ ቦዮችና ኲሬዎች ሁሉ ላይ እንዲዘረጋ ንገረው፤ በዚያን ጊዜ ውሃው ሁሉ ተለውጦ ደም ይሆናል፤ ከእንጨትና ከድንጋይ በተሠሩት የውሃ ማጠራቀሚያ ዕቃዎች እንኳ ሳይቀር በግብጽ ምድር የሚገኘው ውሃ ሁሉ ደም ይሆናል።”
ነገር ግን እምቢ ብትል፥ በዓለም ላይ እኔን የመሰለ ሌላ አምላክ እንደሌለ ታውቅ ዘንድ አንተን ራስህን፥ መኳንንትህንና ሕዝብህን በመቅሠፍቴ ኀይል አሁኑኑ እቀጣለሁ።
ሙሴም ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “ከከተማው እንደ ወጣሁ እጄን ዘርግቼ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ነጐድጓዱም ይቆማል፤ በረዶም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም፤ በዚህ ዐይነት አንተም ምድር የእግዚአብሔር እንደ ሆነች ታውቃለህ።
“እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ተረድታችሁ ታውቁኝና ታምኑብኝ ዘንድ የመረጥኳችሁ አገልጋዮቼና ምስክሮቼ እናንተ ናችሁ። በእርግጥ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ከእዚህ በፊት አልነበረም፤ ወደ ፊትም አይኖርም።