ዘፀአት 8:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም “እንግዲያውስ ነገውኑ ጸልይልኝ” አለ። ሙሴም እንዲህ አለ፤ “እንዳልከው አደርጋለሁ፤ አንተም እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ሌላ አምላክ እንደሌለ በዚያን ጊዜ ታውቃለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖንም፣ “ነገ ይሁን” አለው። ሙሴም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም እንደሌለ ታውቅ ዘንድ አንተ እንዳልኸው ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ክምርም አድርገው ሰበሰቡአቸው፤ ምድሪቱም ገማች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም፥ “ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ታውቅ ዘንድ እሺ እንደ አልህ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም “ነገ” አለ። ሙሴም “አምላካችንን እግዚአብሔርን የሚመስል እንደሌለ ታውቅ ዘንድ እንደ ቃልህ ይሁን። |
“አምላክ ሆይ፥ ከአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅድስናስ እንደ አንተ ያለ ባለግርማ ማን ነው? አንተ ያደረግሃቸውን ተአምራትና አስገራሚ ሥራዎች ሊያደርግ የሚችልስ ማን አለ?
ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “በደስታ እጸልይልሃለሁ፤ ለአንተና ለመኳንንትህ ለሕዝብህም የምጸልይበትን ሰዓት ብቻ ወስንልኝ፤ ከዚያም በኋላ ጓጒንቸሮቹ ከአንተና ከቤትህ ሁሉ ርቀው በዐባይ ወንዝ ብቻ ተወስነው እንዲኖሩ አደርጋለሁ” አለው።
ነገር ግን እምቢ ብትል፥ በዓለም ላይ እኔን የመሰለ ሌላ አምላክ እንደሌለ ታውቅ ዘንድ አንተን ራስህን፥ መኳንንትህንና ሕዝብህን በመቅሠፍቴ ኀይል አሁኑኑ እቀጣለሁ።
ሙሴም ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “ከከተማው እንደ ወጣሁ እጄን ዘርግቼ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ነጐድጓዱም ይቆማል፤ በረዶም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም፤ በዚህ ዐይነት አንተም ምድር የእግዚአብሔር እንደ ሆነች ታውቃለህ።
እኔ ብቻ አምላክ መሆኔንና ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ዕወቁ፤ በቀድሞ ዘመን የተደረጉትን የጥንቱን ነገሮች አስታውሱ፤ እኔ አምላክ ነኝ፤ እኔንም የሚመስል ሌላ የለም።
‘ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ወደ ፊት ከምታደርጋቸው ታላላቅና አስደናቂ ነገሮች ሁሉ ያሳየኸኝ የመጀመሪያውን ክፍል ብቻ እንደ ሆነ ዐውቃለሁ፤ አንተ የምታደርጋቸውን ታላላቅ ነገሮች የሚያደርግ ሌላ አምላክ በሰማይም ሆነ በምድር የለም።
ስለዚህም በላይ በሰማይ፥ በታችም በምድር እግዚአብሔር እርሱ ብቻ አምላክ መሆኑንና ያለ እርሱ ሌላ አምላክ እንደሌለ ዕወቁ፤ በልባችሁም ያዙት።