Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 8:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “በደስታ እጸልይልሃለሁ፤ ለአንተና ለመኳንንትህ ለሕዝብህም የምጸልይበትን ሰዓት ብቻ ወስንልኝ፤ ከዚያም በኋላ ጓጒንቸሮቹ ከአንተና ከቤትህ ሁሉ ርቀው በዐባይ ወንዝ ብቻ ተወስነው እንዲኖሩ አደርጋለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሙሴም ፈርዖንን፣ “በአባይ ወንዝ ካሉት በቀር ከአንተና ከቤቶችህ ጓጕንቸሮቹ እንዲወገዱ ለአንተ፣ ለሹማምትህና ለሕዝብህ የምንጸልይበትን ጊዜ እንድትወስን ለአንተ ትቼዋለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ጌታም እንደ ሙሴ ቃል አደረገ፤ እንቁራሪቶቹም በየቤቶቹ፥ በየመንደሮቹና በሜዳም ሞቱ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሙሴም ፈር​ዖ​ንን፥ “ጓጕ​ን​ቸ​ሮቹ ከአ​ንተ፥ ከሕ​ዝ​ብ​ህም፥ ከቤ​ቶ​ች​ህም እን​ዲ​ጠፉ፥ በወ​ን​ዙም ብቻ እን​ዲ​ቀሩ፥ ለአ​ንተ፥ ለሹ​ሞ​ች​ህም፥ ለሕ​ዝ​ብ​ህም መቼ እን​ድ​ጸ​ልይ ቅጠ​ረኝ” አለው። ፈር​ዖ​ንም፥ “ነገ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሙሴም ፈርዖንን፥ “ጓጕንቸሮቹ ከአንተም ከቤቶችህም እንዲጠፋ፥ በወንዙም ብቻ እንዲቀሩ፥ ለአንተ ለባሪያዎችህም ለሕዝብህም መቼ እንድጸልይ አስታውቀኝ፤” አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 8:9
8 Referencias Cruzadas  

መጥረቢያ እንጨት በሚቈርጥበት በባለቤቱ ላይ መነሣት ይችላልን? መጋዝስ በሚሰነጥቅበት ሰው ላይ መነሣት ይችላልን? እንዲሁም በትር በሚይዘው ሰው ላይ ኀይል አይኖረውም።


ከዚህ በኋላ ኤልያስ የባዓልን ነቢያት “እናንተ ብዙ ስለ ሆናችሁ በመጀመሪያ አንዱን ኰርማ መርጣችሁ በማረድ ወደ አምላካችሁ ጸልዩ፤ ነገር ግን እንጨቱን በእሳት አታቀጣጥሉ” አላቸው።


እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፦ “በምድያማውያን ላይ ድልን አቀዳጃቸው ዘንድ ከአንተ ጋር ያሉ ሰዎች ለእኔ እጅግ ብዙ ሆነዋል፤ በራሳቸው ኀይል የሚያሸንፉ ስለሚመስላቸው ለእኔ ክብር ከመስጠት ይቈጠባሉ፤


ንጉሡም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “ጓጒንቸሮቹን ከእኔና ከሕዝቤ ዘንድ እንዲያርቅ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ፤ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ ሕዝባችሁን እለቃለሁ” አላቸው።


ንጉሡም “እንግዲያውስ ነገውኑ ጸልይልኝ” አለ። ሙሴም እንዲህ አለ፤ “እንዳልከው አደርጋለሁ፤ አንተም እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ሌላ አምላክ እንደሌለ በዚያን ጊዜ ታውቃለህ።


እግዚአብሔርም ወንዙን ከመታ በኋላ ሰባት ቀን አለፈ።


ጓጒንቸሮቹ ከአንተና ከቤትህ ሁሉ፥ ከመኳንንትህና ከሕዝብህም ሁሉ ዘንድ ይወገዳሉ፤ በዐባይ ወንዝ ውስጥ ካልሆነ በቀር፥ በሌላ ቦታ አይገኙም።”


እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “በጠየቅኸው መሠረት ይቅር እላቸዋለሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios