ዘፀአት 40:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም ልክ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ሁሉን ነገር አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ ሁሉንም ነገር ልክ እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ጌታ እንዳዘዘው ሁሉ አደረገ፥ እንዲሁም አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ፤ እንዲሁም አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ አደረገ። |
እነርሱም ካህናት ሆነው ያገለግሉኝ ዘንድ ልክ አባታቸውን በቀባኸው ዐይነት ቀባቸው፤ በመቀባታቸውም ምክንያት በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ካህናት ሆነው ያገለግሉኛል።”
ቀጥሎም ሙሴ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት የአሮንን ወንዶች ልጆች ወደፊት አቅርቦ ቀሚስ አለበሳቸው፤ በወገባቸውም ዙሪያ መታጠቂያ አድርጎ በራሳቸውም ላይ ቆብ ደፋላቸው።
እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ሙሴ የሆድ ዕቃዎቹንና እግሮቹን አጥቦ የአውራ በጉን ሥጋ ሁሉ በመሠዊያው ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቃጠለው፤ ይህም ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ነበር።
በራሱም ላይ ጥምጥም አደረገለት፤ በጥምጥሙም ላይ ከፊት ለፊት በኩል እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በወርቅ አጊጦ የተሠራውን የቅድስና ምልክት የሆነውን አክሊል አኖረ።
ሁለት ቀንም ይሁን አንድ ወር፥ አንድ ዓመትም ይሁን ከዚያ የረዘመ ጊዜ ደመናው በድንኳኑ ላይ እስካረፈበት ጊዜ ድረስ አይንቀሳቀሱም ነበር፤ ደመናው ሲነሣ ግን ጒዞአቸውን ይቀጥሉ ነበር።
ከዚህ በኋላ ሙሴ ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “እስራኤል ሆይ፥ አሁን እንግዲህ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ ለመውረስ ያበቃችሁ ዘንድ የማስተምራችሁን ሕግና ሥርዓት አዳምጣችሁ በሥራ ላይ አውሉት።