እግዚአብሔርም “ሕይወት ሰጪ የሆነ መንፈሴ ከሰዎች ጋር ለዘለዓለም አይኖርም፤ ሰዎች ሟቾች ስለ ሆኑ ከእንግዲህ ወዲያ ከ 120 ዓመት የበለጠ አይኖሩም” አለ።
ዘፀአት 4:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገናም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ አሁን ወደ ግብጽ መመለስህ ስለ ሆነ፥ በሰጠሁህ ኀይል የምታደርጋቸውን ተአምራት በፈርዖን ፊት መፈጸም እንዳለብህ አትዘንጋ፤ ሆኖም እኔ የፈርዖንን ልብ ስለማደነድን ሕዝቡን በቀላሉ አይለቅም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ወደ ግብጽ በምትመለስበት ጊዜ በሰጠሁህ ኀይል የምትሠራቸውን ታምራት ሁሉ በፈርዖን ፊት መፈጸም እንዳለብህ አትዘንጋ። እኔ ግን ሕዝቡን እንዳይለቅ ልቡን አደነድነዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን አለው፦ “ወደ ግብጽ ስትመለስ በእጅህ ያደረግሁትን ተአምራት ሁሉ ተመልከት በፈርዖንም ፊት ታደርጋቸዋለህ፤ እኔም ልቡን አጸናዋለሁ፥ ሕዝቡንም አይለቅቅም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ግብፅ ተመልሰህ ስትሄድ በእጅህ ያደረግሁትን ተአምራቴን ሁሉ በፈርዖን ፊት ታደርገው ዘንድ ተመልከት፤ እኔ ግን ልቡን አጸናዋለሁ፤ ሕዝቡንም አይለቅቅም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ “ወደ ግብፅ ስትመለስ በእጅህ ያደረግሁትን ተአምራት ሁሉ በፈርዖን ፊት ታደርገው ዘንድ ተመልከት፤ እኔ ግን ልቡን አጸናዋለሁ፤ ሕዝቡንም አይለቅቅም። |
እግዚአብሔርም “ሕይወት ሰጪ የሆነ መንፈሴ ከሰዎች ጋር ለዘለዓለም አይኖርም፤ ሰዎች ሟቾች ስለ ሆኑ ከእንግዲህ ወዲያ ከ 120 ዓመት የበለጠ አይኖሩም” አለ።
እግዚአብሔርም ‘እንዴት አድርገህ ልታሳስተው ትችላለህ?’ አለው። መንፈሱም ‘ሄጄ የአክዓብ ነቢያት ሁሉ ሐሰት እንዲናገሩ አደርጋለሁ’ ሲል መለሰለት፤ እግዚአብሔርም ‘እንግዲያውስ ሄደህ አሳስተው፤ ይከናወንልሃል አለው።’ ”
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እነሆ እንደገና ወደ ፈርዖን ተመልሰህ ግባ፤ እኔ የእርሱንና የመኳንንቱን ልብ ያደነደንኩት በመካከላቸው እነዚህን ተአምራት ለማድረግ ዐቅጄ ነው፤
ሙሴና አሮንም እነዚህን ተአምራት በንጉሡ ፊት አደረጉ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የንጉሡን ልብ ስላደነደነ እስራኤላውያን ከምድሪቱ እንዲወጡ አልፈቀደላቸውም።
እኔም ልቡን ስለማደነድነው ያሳድዳችኋል፤ ስለዚህም በንጉሡና በሠራዊቱ ላይ የምጐናጸፈው ድል ለእኔ ክብር ይሆናል፤ በዚያን ጊዜ ግብጻውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።” እስራኤላውያንም እንደ ተነገራቸው አደረጉ።
ስለዚህም እጅግ አስፈሪ የሆኑ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ የኀይል ክንዴን ዘርግቼ ግብጻውያንን እቀጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ እንድትወጡ ይፈቅድላችኋል።
ጓጒንቸሮቹ ከአንተና ከቤትህ ሁሉ፥ ከመኳንንትህና ከሕዝብህም ሁሉ ዘንድ ይወገዳሉ፤ በዐባይ ወንዝ ውስጥ ካልሆነ በቀር፥ በሌላ ቦታ አይገኙም።”
ቀጥሎም “እንዳያዩ፥ እንዳይሰሙና እንዳያስተውሉ በዓይናቸው ተመልክተው፥ በጆሮአቸው ሰምተው፥ በልባቸው አስተውለው ወደ እኔ ተመልሰው እንዳይፈወሱ ይህን ሕዝብ ልቡ የደነደነ፥ ጆሮው የተደፈነ፥ ዐይኑም የተጨፈነ እንዲሆን አድርግ” አለኝ።
አምላክ ሆይ! ለምን መንገድህን እንድንስት አደረግኸን? እንዳንፈራህስ ለምን ልባችንን አደነደንክ? ለአገልጋዮችህ፥ የአንተ ስለ ሆኑት ነገዶች ስትል እባክህ ተመለስ።
በአርኖን ሸለቆ ጠረፍ ከምትገኘው ከአሮዔርና በሸለቆው ከሚገኘው ከተማ ጀምሮ እስከ ገለዓድ ድረስ እኛን ሊቋቋመን የሚችል ከተማ አልነበረም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉንም አሳልፎ ሰጠን።
እነዚህም ሁሉ ከእስራኤላውያን ጋር ጦርነት እንዲገጥሙ እግዚአብሔር ልባቸውን እልኸኛ አድርጎ አነሣሣቸው። ስለዚህም በአጠቃላይ እንዲደመሰሱ ተፈርዶባቸው ያለ ምሕረት ተገደሉ፤ እግዚአብሔርም አስቀድሞ ለሙሴ የሰጠው ትእዛዝ ይኸው ነበር።
ደግሞም፥ “እነሆ! ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ፤ እነሆ! ሰዎችን አደናቅፎ የሚጥል አለት” ይላል። እነርሱ ቃሉን ባለማመናቸው ይሰናከላሉ፤ አስቀድመውም ለዚህ የተመደቡ ናቸው።