በመጪው ዘመን የሚወለድ ወንድ ልጅ ሁሉ በተወለደ በስምንተኛው ቀን ይገረዝ፤ እንዲሁም በቤትህ የተወለዱና በቤትህ ሳይወለዱ ከውጪ በገንዘብ ተገዝተው የመጡ ባሪያዎች ሳይቀሩ በዚሁ ዐይነት ይገረዙ።
ዘፀአት 22:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከቀንድ ከብቶችህ፥ ከበጎችህም በኲር ሆነው የሚወለዱትን ለእኔ አቅርብ፤ ይኸውም በኲር ሆኖ የተወለደ ወንድ ሁሉ ለሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቈይ፤ በስምንተኛው ቀን ለእኔ ታቀርበዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከቀንድ ከብትህና ከበጎችህም እንዲሁ አድርግ፤ ለሰባት ቀን ከእናቶቻቸው ጋራ ይቈዩ፤ በስምንተኛው ቀን ግን ለእኔ ሰጠኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅዱስ ወገን ትሆኑልኛላችሁ፤ ስለዚህ በሜዳ አውሬ የገደለውን ሥጋ አትብሉ፤ ለውሻ ጣሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም በበሬዎችህና በበጎችህ፥ በአህያህም ታደርገዋለህ፤ ሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቀመጥ፤ በስምንተኛውም ቀን ለእኔ ትሰጠዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም በበሬዎችህና በበጎችህ ታደርገዋለህ፤ ሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቀመጥ፥ በስምንተኛውም ቀን ለእኔ ትሰጠዋለህ። |
በመጪው ዘመን የሚወለድ ወንድ ልጅ ሁሉ በተወለደ በስምንተኛው ቀን ይገረዝ፤ እንዲሁም በቤትህ የተወለዱና በቤትህ ሳይወለዱ ከውጪ በገንዘብ ተገዝተው የመጡ ባሪያዎች ሳይቀሩ በዚሁ ዐይነት ይገረዙ።
እኔም እንዲህ ስል መለስኩ፦ “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ይህስ ከቶ አይሁን! እኔ ከቶ ረክሼ አላውቅም፤ ከሕፃንነቴ ጀምሮ የበከተ ወይም አውሬ የገደለው ከብትን ሥጋ የበላሁበት ጊዜ የለም፤ ጸያፍ ምግብም አልበላሁም።”
እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ እኔ ቅዱስ ስለ ሆንኩ እናንተም ራሳችሁን የተቀደሰ አድርጉ፤ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱትን ነፍሳት በመብላት ራሳችሁን አታርክሱ።
“ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም የውጪ አገር ተወላጅ የሆነ ሰው፥ ሞቶ የተገኘውን ወይም አውሬ የገደለውን የእንስሳ ሥጋ ቢበላ ልብሱን አጥቦ፥ ሰውነቱንም ታጥቦ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል፤
“እንቦሳ፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ሲወለድ ሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቀመጥ፤ ከስምንተኛው ቀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ መቅረብ ይችላል።
“ሞቶ የተገኘውን እንስሳ አትብላ፤ በመካከልህ የሚኖሩ የውጪ አገር ሰዎች እንዲመገቡት ፍቀድላቸው፤ ወይም ለውጪ አገር ሰዎች በዋጋ ልትሸጥላቸው ትችላለህ። አንተ ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተለየህ ሕዝብ ነህ። “የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።
“ከከብትህ ወይም ከበግህ መንጋ የሚወለደውን ወንድ የሆነ በኲር ሁሉ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አድርግ፤ በኲር የሆኑትን በሬዎች ለማንኛውም ተግባር አትጠቀምባቸው፤ እንዲሁም ከበጎች መንጋ በኲሮችን ጠጒራቸውን አትሸልት፤