ከዚህ በኋላ አብራም ሎጥን እንዲህ አለው፤ “እኛ ወንድማማች ስለ ሆንን በእኔና በአንተ መካከል እንዲሁም በእኔ እረኞችና በአንተ እረኞች መካከል ጠብ ሊነሣ አይገባም፤
ዘፀአት 2:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውየውም “አንተን በእኛ ላይ ገዢና ዳኛ አድርጎ የሾመህ ማን ነው? ወይስ ያንን ግብጻዊ እንደ ገደልክ እኔንም መግደል ትፈልጋለህን?” አለው፤ ሙሴም እጅግ ፈርቶ “ያደረግኹት ነገር ታውቋል ማለት ነው” ብሎ አሰበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየውም፣ “አንተን በእኛ ላይ ገዥና ዳኛ አድርጎ የሾመህ ማን ነው? ግብጻዊውን እንደ ገደልኸው እኔንም ልትገድለኝ ትፈልጋለህን?” አለው። ሙሴም፣ “ለካስ ያደረግሁት ነገር ታውቋል!” በማለት ፈራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሱም፦ “አንተን በእኛ ላይ አለቃና ዳኛ አድርጎ የሾመህ ማን ነው? ግብፃዊውን እንደ ገደልኸው ልትገድለኝ ትፈልጋለህን?” አለው። ሙሴም፦ “በእውነት ይህ ነገር ታውቆአል” ብሎ ፈራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሙን የሚበድለው ያም ሰው፥ “በእኛ ላይ አንተን አለቃ ወይስ ዳኛ ማን አደረገህ? ወይስ ግብፃዊውን ትናንት እንደ ገደልኸው ልትገድለኝ ትሻለህን?” አለው። ሙሴም፥ “በእውነት ይህ ነገር ታውቆአልን?” ብሎ ፈራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያም፦ “በእኛ ላይ አንተን አለቃ ወይስ ዳኛ ማን አደረገህ? ወይስ ግብፃዊውን እንደገደልኸው ልትገድለኝ ትሻለህን?” አለው። ሙሴም፦ “በእውነት ይህ ነገር ታውቆአል” ብሎ ፈራ። |
ከዚህ በኋላ አብራም ሎጥን እንዲህ አለው፤ “እኛ ወንድማማች ስለ ሆንን በእኔና በአንተ መካከል እንዲሁም በእኔ እረኞችና በአንተ እረኞች መካከል ጠብ ሊነሣ አይገባም፤
ሰዎቹ ግን “አንተ ስደተኛ፥ ሂድ ወዲያ! ለመሆኑ ልናደርገው የሚገባንን ነገር የምትነግረን አንተ ማን ነህ? ሂድ ወዲያ፤ አለበለዚያ በእነርሱ ላይ ልናደርግ ካሰብነው የከፋ ነገር በአንተ ላይ እናደርጋለን” አሉት። በዚህ ዐይነት ሎጥን ወዲያ ገፍትረው በሩን ለመስበር ተነሣሡ፤
እነርሱም በሙሴና በአሮን ፊት ተሰብስበው እንዲህ አሉአቸው፦ “እናንተ ከልክ አልፋችኋል! የዚህ ጉባኤ አባላት የሆኑ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለዩ ናቸው፤ እግዚአብሔርም ከእኛ ሁሉ ጋር ነው፤ ታዲያ በእግዚአብሔር ጉባኤ ላይ ራሳችሁን ከፍ ከፍ የምታደርጉት ስለምንድን ነው?”
ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ያስተምር ነበር። በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች ወደ እርሱ ቀረቡና “ይህን ሁሉ የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ይህን ሥልጣን የሰጠህስ ማን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።
“የእስራኤል ሕዝብ ሙሴን ‘በእኛ ላይ ገዢና ፈራጅ እንድትሆን ያደረገህ ማን ነው?’ በማለት ተቃውመውት ነበር፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ይህንኑ ሙሴን በቊጥቋጦው ውስጥ በተገለጠለት መልአክ አማካይነት ገዢና ነጻ አውጪ አድርጎ ወደ እነርሱ ላከው።