ቤተሰቡ አነስተኛ ከመሆኑ የተነሣ እንስሳውን በልቶ ለመጨረስ የማይችል ከሆነ ግን እርሱና የቅርብ ጐረቤቱ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ሊመገበው የሚችለውን ያኽል ተመጥኖ እንስሳውን በአንድነት አብረው ይብሉት።
ዘፀአት 12:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምትመርጡት እንስሳ በግ ወይም ፍየል መሆን ይችላል፤ ነገር ግን ምንም ነውር የሌለበትና አንድ ዓመት የሞላው ተባዕት ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምትመርጡት ጠቦት በግ ወይም ፍየል ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ምንም ነቀፋ የሌለበትና አንድ ዓመት የሞላው ተባዕት መሆን አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእናንተ ጠቦት ነውር የሌለበት፥ ተባዕት፥ የአንድ ዓመት ይሁን፤ ከበጎች ወይም ከፍየሎች ውሰድ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለእናንተ ይሁን፤ ከበጎች ወይም ከፍየሎች ውሰዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእናንተ ጠቦት ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ይሁን፤ ከበጎች ወይም ከፍየሎች ውሰድ። |
ቤተሰቡ አነስተኛ ከመሆኑ የተነሣ እንስሳውን በልቶ ለመጨረስ የማይችል ከሆነ ግን እርሱና የቅርብ ጐረቤቱ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ሊመገበው የሚችለውን ያኽል ተመጥኖ እንስሳውን በአንድነት አብረው ይብሉት።
ይኸውም ከቀንድ ከብቱ መካከል አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ቢፈልግ ምንም ነውር የሌለበትን ኰርማ መርጦ ያምጣ፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት የሰመረ መሥዋዕት ይሆንለት ዘንድ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር በኩል ያቅርበው።
የእህል መባችሁን በምታቀርቡበት በዚያኑ ቀን ነውር የሌለበትና አንድ ዓመት የሆነውን የበግ ጠቦት የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ አብራችሁ አቅርቡ።
እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በሕዝቦች ዘንድ የተከበረስለሆነ፥ ከበግ መንጋዎቹ መካከል አውራ በግ እያለው ለተሳለው ስለት ነውር ያለበትን በግ መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ የተረገመ ነው!” ይላል የሠራዊት አምላክ።
“ከከብት ወይም ከበግ መንጋዎች መካከል አንዳች ነውር ያለበትን እንስሳ ለእግዚአብሔር ለአምላክህ መሥዋዕት አድርገህ አታቅርብ፤ ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው።