Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 12:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ቤተሰቡ አነስተኛ ከመሆኑ የተነሣ እንስሳውን በልቶ ለመጨረስ የማይችል ከሆነ ግን እርሱና የቅርብ ጐረቤቱ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ሊመገበው የሚችለውን ያኽል ተመጥኖ እንስሳውን በአንድነት አብረው ይብሉት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ማንኛውም ቤተ ሰብ ለአንድ ሙሉ ጠቦት ቍጥሩ አነስተኛ ከሆነ፣ በጎረቤት ያሉትን ሰዎች ቍጥር እስከ ቅርብ ከሆነው ጋራ መካፈል ይኖርበታል፤ እያንዳንዱ ሰው በሚበላው መጠንም ምን ያህል ጠቦት እንደሚያስፈልግ መወሰን ይኖርባችኋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የቤተሰቡ ቍጥር ም ለጠቦቱ የሚያንስ ከሆነ እርሱና ለቤቱ የቀረበው ጎረቤቱ በእያንዳንዱ ሰው ቍጥር አንድ ጠቦት ይውሰድ፤ እያንዳንዱም እንደሚበላው መጠን ከጠቦቱ ይካፈሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በቤት ያሉት ሰዎች ጥቂት ቢሆኑ፥ አንድ በግም የማ​ይ​ጨ​ርሱ ቢሆኑ በጉን ሊጨ​ርሱ በሚ​በቁ በሰ​ዎች ቍጥር እያ​ን​ዳ​ንዱ በአ​ጠ​ገቡ የሚ​ኖ​ረ​ውን ጎረ​ቤ​ቱን ይው​ሰድ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የቤቱ ሰዎች ቁጥርም ጠቦቱን ለመጨረስ የማይበቃ ቢሆን እርሱና ለቤቱ የቀረበው ጎረቤቱ እንደ ነፍሶቻቸው ቁጥር አንድ ጠቦት ይውሰድ፤ እያንዳንዱም እንደሚበላው መጠን ከጠቦቱ ይካፈሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 12:4
4 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ እኔ አሁን የሰማንያ ዓመት ሰው ነኝ፤ የሚያስደስቱና የማያስደስቱ ነገሮችን መለየት እችላለሁን? የምበላውንም ሆነ የምጠጣውን ጣዕም መለየት እችላለሁን? ጆሮዬም የወንድና የሴት ዘፋኞችን ድምፅ መስማት ይችላልን? ንጉሥ ሆይ! በጌታዬ ላይ ለምን ተጨማሪ ሸክም እሆንብሃለሁ?


ለመላው የእስራኤል ሕዝብ ይህን ሥርዓት አስተምሩ፤ ይህ ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን እያንዳንዱ ሰው በቤተሰቡ ደረጃ አንድ ጠቦት ይምረጥ።


የምትመርጡት እንስሳ በግ ወይም ፍየል መሆን ይችላል፤ ነገር ግን ምንም ነውር የሌለበትና አንድ ዓመት የሞላው ተባዕት ይሁን።


ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ የፋሲካውንም ራት አዘጋጁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos