ኤፌሶን 4:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተቈጡ! በቊጣችሁ ግን ኃጢአት አትሥሩ፤ ቊጣችሁም ሳይወገድ ፀሐይ አይጥለቅባችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ተቈጡ፤ ነገር ግን ኀጢአት አትሥሩ፤” በቍጣችሁ ላይ ፀሓይ አይግባ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተቆጡ፥ ኃጢአትን ግን አታድርጉ፤ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተቈጡ፤ አትበድሉም፤ ፀሐይ ሳይጠልቅም ቍጣችሁን አብርዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤ |
ሙሴም “መኳንንትህ ሁሉ ወደ እኔ መጥተው እጅ ይነሡኛል፤ ሕዝቤንም ይዤ እንድወጣ ይለምኑኛል፤ ከዚያም በኋላ እሄዳለሁ” በማለት ንግግሩን አበቃ፤ ይህንንም ከተናገረ በኋላ በታላቅ ቊጣ ከንጉሡ ፊት ወጥቶ ሄደ።
“አሮን ለእስራኤላውያን ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር አይገባም፤ እናንተ ሁለታችሁ በመሪባ ውሃ ዘንድ በትእዛዜ ላይ ስላመፃችሁ አሮን ይሞታል።
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በወንድሙ ላይ የሚቈጣ ሁሉ ይፈረድበታል፤ ደግሞም ወንድሙን፥ ‘አንተ የማትረባ!’ ብሎ የሚሳደብ በሸንጎ ይፈረድበታል፤ ‘ደደብ!’ ብሎ የሚሳደብ ሁሉ በገሃነመ እሳት ይፈረድበታል።
ኢየሱስም ይህን በማየት ተቈጥቶ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “የእግዚአብሔር መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ስለ ሆነች ሕፃናት ወደ እኔ ይምጡ፤ ተዉ፤ አትከልክሉአቸው፤
ኢየሱስም ስለ ልባቸው ድንዛዜ አዝኖ በዙሪያው ያሉትን በቊጣ ተመለከተና ሰውየውን፦ “እጅህን ዘርጋ” አለው። እርሱም በዘረጋ ጊዜ እጁ ዳነለት።
እርሱ ድኻ በመሆኑ ያን ገንዘብ ለማግኘት በብርቱ ጒጉት ስለሚጠብቅ በየቀኑ የሠራበትን ገንዘብ ፀሐይ ከመጥለቅዋ በፊት ስጠው፤ ባትከፍለው ግን ወደ እግዚአብሔር በመጮኽ ያሳጣሃል፤ አንተም በደለኛ ሆነህ ትገኛለህ።
ዮናታንም በቊጣ ከማእዱ ላይ ተነሣ፤ በዚያ ቀን ማለትም አዲስ ጨረቃ በታየችበት በዓል በሁለተኛ ቀን ምንም ምግብ አልበላም፤ ሳኦል ዳዊትን በማዋረዱ ምክንያት ስለ ዳዊት ሁኔታ ዮናታን በብርቱ አዝኖ ነበር።