መክብብ 5:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተስለህ የማትፈጽመው ከሆነ ግን ቀድሞውንም ባትሳል የተሻለ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስእለት ተስሎ ካለመፈጸም፣ አለመሳል ይሻላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አፍህ ወደ ኃጢአት እንዲወስድህ አትፍቀድለት፥ በመልአክም ፊት፦ ስሕተት ነበረ አትበል፥ እግዚአብሔር በቃልህ ለምን ይቈጣ? ለምንስ የእጅህንም ሥራ ያጥፋ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተስለህ የማትፈጽም ከሆነ ባትሳል ይሻላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተስለህ የማትፈጽም ብትሆን ባትሳል ይሻላል። |
“አንድ ሰው ለክፉም ሆነ ለደግ ስለ ምንም ነገር ያለ ጥንቃቄ በግዴለሽነት ስእለት ቢሳል፥ ያደረገውን ስሕተት ካወቀበት ጊዜ አንሥቶ በደል ይሆንበታል።
ሳትሸጠው በፊት መሬቱ የአንተ አልነበረምን? ከሸጥከውስ በኋላ ገንዘቡ የአንተው አልነበረምን? ታዲያ፥ ይህን ነገር ስለምን በልብህ አሰብክ? የዋሸኸው በእግዚአብሔር ላይ ነው እንጂ በሰው ላይ አይደለም።”
“ለእግዚአብሔር አምላክህ ስእለት በምታደርግበት ጊዜ ለመስጠት ወይም ለመፈጸም ቃል የገባህበትን ስእለት አታዘግይ፤ እግዚአብሔር አንተ የገባኸውን ቃል እንድትፈጽም ይፈልጋል፤ ስእለትህን ካልፈጸምክ ግን ኃጢአት ይሆንብሃል።
ባያትም ጊዜ በሐዘን ልብሱን በመቅደድ “ወዮ ልጄ! ልቤን በሐዘን ሰበርሽው! ለታላቅ ጭንቀትም ዳረግሽኝ፤ ለእግዚአብሔር ቃል ገብቼአለሁና ስለቴን ልመልሰውም አልችልም፤” አለ።