ያዕቆብም “ምንም ቢሆን ከእናንተ ጋር አይሄድም፤ ወንድሙ ሞቶአል፤ የቀረው እርሱ ብቻ ነው፤ በመንገድ አንድ ጒዳት ቢደርስበት በእርጅናዬ ዘመን በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር እንድወርድ ታደርጉኛላችሁ” አላቸው።
መክብብ 12:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ከፍተኛ ስፍራዎች መውጣት ያስፈራሃል፤ በእግር መጓዝም አደገኛ ይሆንብሃል፤ ጠጒርህ እንደ ለውዝ አበባ ነጭ ይሆናል፤ ራስህን ችለህ መራመድ አቅቶህ እንደ አሮጌ ኩብኩባ ትጐተታለህ፤ ፍላጎትህ መቀስቀሱ ይቀራል። ድምፅ እንኳ ከእንቅልፍህ ይቀሰቅስሃል። ሰውም ወደ ዘለዓለማዊ መኖሪያው ይሄዳል፤ አልቃሾችም በየመንገዱ እያለቀሱ ይሸኙታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳገት መውጣት ሲያርድ፣ መንገድም ሲያስፈራ፣ የአልሙን ዛፍ ሲያብብ፣ አንበጣም ራሱን ሲጐትት፣ ፍላጎት ሲጠፋ፤ በዚያም ጊዜ ሰው ወደ ዘላለማዊ ቤቱ ይሄዳል፤ አልቃሾችም በአደባባዮች ይዞራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፍ ያለውን ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፥ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፈቃድም ሲጠፋ፥ ሰው ወደ ዘለዓለም ቤት ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፍ ያለውን ተመልክተው ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፤ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፍሬም ሳይበተን፤ ሰው ወደ ዘለዓለም ቤቱ ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፍ ያለውን ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፥ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፈቃድም ሲጠፋ፥ ሰው ወደ ዘላለም ቤት ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፥ |
ያዕቆብም “ምንም ቢሆን ከእናንተ ጋር አይሄድም፤ ወንድሙ ሞቶአል፤ የቀረው እርሱ ብቻ ነው፤ በመንገድ አንድ ጒዳት ቢደርስበት በእርጅናዬ ዘመን በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር እንድወርድ ታደርጉኛላችሁ” አላቸው።
አርጅታችሁ ጠጒራችሁ እስከሚሸብትበት ጊዜ ድረስ፥ የምጠብቃችሁ እኔ ነኝ፤ ፈጥሬአችኋለሁ፤ እንከባከባችኋለሁም፤ እረዳችኋለሁ፤ ከክፉ ነገርም እጠብቃችኋለሁ።