Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 19:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 “በዕድሜ የገፉ ሽማግሌዎች ሲመጡ ስታይ ከተቀመጥክበት በመነሣት አክብራቸው፤ እኔን አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 “ ‘ዕድሜው ለገፋ ተነሥለት፤ ሽማግሌውን አክብር፤ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 “በአዛውንት ፊት ተነሣ፥ ሽማግሌውንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ ጌታ ነኝ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 “በሽ​በ​ታሙ ፊት ተነሣ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንም አክ​ብር፤ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ፍራ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 በሽበታሙ ፊት ተነሣ፥ ሽማግሌውንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 19:32
15 Referencias Cruzadas  

ሽማግሌን እንደ አባት አድርገህ ምከረው እንጂ አትገሥጸው፤ ወጣቶች ወንዶችን እንደ ወንድሞች፥


መሪዎች እጆቻቸው ታስረው ተንጠለጠሉ፤ ሽማግሌዎችም አልተከበሩም።


ሽበት የክብር ዘውድ ነው። የሚገኘውም በተቀደሰ አኗኗር ነው።


የወጣቶች መመኪያ ብርታታቸው ነው፤ የሽማግሌዎችም መከበሪያ ሽበታቸው ነው።


ቡዛዊው የባራኪ ልጅ ኤሊሁ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ በዕድሜዬ ከእናንተ ያነስኩ በመሆኔና እናንተም አዛውንት በመሆናችሁ፥ ኀፍረትና ፍርሀት ተሰምቶኝ ሐሳቤን ሳልገልጥ እስከ አሁን ቈይቼ ነበር።


ኤሊሁ በዕድሜ ከሌሎቹ ያነሰ በመሆኑ ሁሉም ተናግረው እስከሚጨርሱ ድረስ በተራው ከኢዮብ ጋር ለመናገር ይጠባበቅ ነበር።


ሰውን ሁሉ አክብሩ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።


እንግዲህ ለበላይ ባለሥልጣን ሊደረግ የሚገባውን ሁሉ አድርጉ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን ክፈሉ፤ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።


ሕዝቡም እርስ በርሱ አንዱ ሌላውን ለመጨቈን ባልንጀራ በባልንጀራው ላይ ይነሣሣል፤ ወጣቱ ሽማግሌውን አያከብርም፤ ተንቆ ይኖር የነበረውም ሰው ክብር ባለው ሰው ላይ ይታበያል።


ደንቆሮውን አትስደብ፤ ዐይነ ዕውሩንም ለማሰናከል በፊቱ እንቅፋት አታኑር፤ አምላክህን ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ።


ስለዚህም ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጉዳይ ልትነግር ወደ ንጉሡ ገባች፤ ንጉሡም ከተቀመጠበት ተነሥቶ እናቱን እጅ በመንሣት ተቀበላት፤ እርሱም በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት፤


ራሔልም አባቷን “ጌታዬ በወር አበባዬ ምክንያት መነሣት ስላልቻልኩ ቅር አትሰኝብኝም” አለችው። ላባ በሁሉ ስፍራ ፈልጎ ጣዖቶቹን ማግኘት አልቻለም።


በታላቅ ኀይልና በሥልጣን ከግብጽ ምድር ላወጣኋችሁ ለእኔ ለእግዚአብሔር ታዛዦች ሁኑ፤ መስገድና መሥዋዕት ማቅረብ የሚገባችሁ ለእኔ ብቻ ነው፤


የወለደህ እርሱ ስለ ሆነ የአባትህን ምክር ስማ፤ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።


ዮሴፍ ልጆቹን ከያዕቆብ ጒልበት ፈቀቅ አደረገና ወደ መሬት ጐንበስ ብሎ ሰገደ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios