ዘዳግም 7:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከበሽታ ሁሉ ይጠብቅሃል፤ በግብጽ አገር በነበርክ ጊዜ ካየኸው አሠቃቂ በሽታ ሁሉ ማንኛውንም በአንተ ላይ አያመጣም፤ ነገር ግን እነዚህን በሽታዎች በሚጠሉህ ላይ ያመጣባቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከማናቸውም በሽታ ነጻ ያደርግሃል፤ በግብጽ የምታውቃቸውን እነዚያን አሠቃቂ በሽታዎች በሚጠሉህ ሁሉ ላይ እንጂ በአንተ ላይ አያመጣብህም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሕማምን ሁሉ ከአንተ ያርቃል፥ የምታውቀውንም ክፉውን የግብጽ በሽታ ሁሉ በአንተ ላይ አያደርስብህም፥ በሚጠሉህ ሁሉ ላይ ግን ያመጣባቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግብፃውያን ላይ ሲመጣ ያየኸውን ክፉ ሕማምና ደዌ ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ያርቅልሃል፤ ያየኸውንም መከራ ሁሉ ወደ አንተ አያመጣውም፤ ከአንተም በሚጠሉህ ሁሉ ላይ ይመልሰዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሕማምን ሁሉ ከአንተ ያርቃል፤ የምታውቀውንም ክፉውን የግብፅ በሽታ ሁሉ በአንተ ላይ አያደርስብህም፥ በጠላቶችህም ሁሉ ላይ ያመጣባቸዋል። |
እንዲህም አላቸው፤ “በጥሞና ትእዛዞቼን ብታዳምጡና በፊቴ መልካም የሆነውን ነገር በታዛዥነት ብታደርጉ፥ ኅጎቼንም ሁሉ ብትጠበቁ፥ በግብጻውያን ላይ ካመጣሁባቸው በሽታዎች በአንዱ እንኳ አልቀጣችሁም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
በግብጽ ምድር ላይ በወረደ ጊዜ አይተህ ትፈራው የነበረውን ያን አሠቃቂ በሽታ ሁሉ እንደገና በአንተ ላይ ይልካል፤ ከዚያም ደዌ አትፈወስም፤